ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
67

በምሥራቅ ጎጃም ዞን በአነደድ ወረዳ የአምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማዉ ዉስጥ ለዉስጥ ያለውን መንገድ ማሰራት እንዲሁም ይህን መንገድ ለማሰራት የማሽነሪ ኪራይ ይፈለጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ማሽነሪዎች ያላችሁ እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡- 1. ግሪደር ፣ 2. ኤክስካቫተር ፣3. ሩሎ ፣ 4. ሻወር ትራክ እና 5. ገልባጭ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳድር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. የኪራይ መጠን ከ200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል አምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች ኦርጅናል የጨረታ ሃሳባቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአንድ ፖስታ ፤ኮፒ የጨረታ ሃሳብ በአንድ ፖስታ በማድረግ ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ፖስታ በጥንቃቄ አሽገው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተምና አድራሻውን በመሙላት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በአነደድ ወረዳ በአምበር ከተማ መሪ ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥን በዚሁ ዕለት 3፡30 ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡00 ላይ በአነ/ወ/አ/ከ/መ/ማ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 የሚከፈት ሆኖ 21ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ጨረታውን ከመክፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ያልተገኙ ተጫራቾች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  8. በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚይዝበት ወቅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ያሸነፉበትን ንብረት ጠቅላላ ወጭውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ አምበር ከተማ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  10. ውድድሩ በጠቅላላ ዋጋ (በሎት ውድድር) ነው፡፡
  11. መሥሪያ ቤቱ ከቀረበው አጠቃላይ የሥራ መጠን /ዋጋ ላይ እስከ ሃያ በመቶ መቀነስ እና መጨመር ይችላል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በክፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ አምበር ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 261 00 12 እና 058 261 07 12 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአምበር ከተማ መሪ መዘጋጃ ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here