በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ድን በ2017 ዓ/ም በመደበኛ በጀት እና በስፖርት ምክር ቤት በጀት ለስማዳ ወረዳ መንገድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሥር ከወገዳ ቄስውሃ ፈንቶሜዳ እና ከወገዳ ሰኞ ገበያ አስፋሜዳ ለሚያሰራዉ መንገድ የጠጠር ማልበስ ሥራ ለማስራት ሎት 1 ሮሎ እና ግሬደር ማሽን እና ሎት 2 የስፖርት እቃና አልባሳት በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ለማሽኑ ነዳጅን ጨምሮ ማንኛውንም ወጭ በጨረታ አሸናፊ የሚሸፈን ይሆናል፡፡ በመሆኑም፡- ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች
- ህጋዊ /ወቅታዊ/ የታደሰ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ስማዳ ወረዳ ግ/ን/አስደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ስማቸውን ፊርማቸውን ማህተማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
- የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ /ማሻሻያ/ ማድረግና ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችለም ሥርዝ ድል ፍፁም የተከለከለ ነዉ፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የባለቤትነት የሚገልጽ ሊብሬ ኮፒዉን በዉል ጊዜ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 01 67 ደውሎ ወይም ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 27 በአካል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት