ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
131

በሰሜን ጎንደር ዞን የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል የግንባታ እቃዎችን በሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ የጨረታው አይነት የግንባታ እቃዎች፤ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይገባቸዋል፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት/ ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
  4. ከተ.ቁ 1-3 የተጠየቀውን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት የሚነበብ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ አለባቸው፡፡
  5. የጨረታ ሰነድ የሚሸጠው ጨረታው ከወጣበት ከ24/10/2016 ዓ.ም እስከ 8/11/2016 ዓ.ም ድረስ ለ15 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ቆይታ ይኖረዋል፡፡
  6. ጨረታው በቀን 8/11/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4፡00 በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 62 ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ላይ ተጨራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ 30.00 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል በደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል ቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት መግዛት ይቻላል፡፡
  8. የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ የሌለበት እና በሰነዱ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን እና የድርጅቱ ማህተም መቀመጥ አለበት፡፡
  9. ጨረታው የሚታየው በሎት ስለሆነ ከጨረታ ሰነዱ ያሉ ሁሉንም እቃዎች መሞላት ይኖርባቸዋል እዲሁም የሚሞሉት የጨረታ ሰነዶች በኦርጅናል ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብረዉ መግባት ይኖርበታል፡፡
  10. የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ሂ1 ጥቅል ዋጋ 3,000.00 /ሦስት ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ጥሬ ገንዘብ ሆነ ቼክ አያይዞ ከጨረታ ሳጥኑ ማስገባት ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  11. ጨረታውን ሆን ተብሎ ለማደናቀፍ የሚደረግ የዋጋ አሞላል ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን መታወቅ አለበት፡፡
  12. አሸናፊ ድርጅት የግንባታ እቃዎቹን ውል እንዲወስድ በተጠየቀ ጊዜ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በፍትህ ፊት ቀርቦ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  13. አሸናፊ ድርጅት የግንባታ እቃዎቹን ደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል በማምጣት እስቶር የሚያስረክብ መሆን አለበት፡፡
  14. የጨረታ መዝጊያ ጊዜው ከተጠናቀቀ በኋላ የሚመጣ ፖስታ ዋጋ አይኖረውም፡፡
  15. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  16. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 117 05 12 ወይም 058 117 00 39 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

የደባርቅ ጠቅላላ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here