በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት መሬት ቢሮ በካልም ፕሮጀክት እና በተዘዋዋሪ ፈንድ በጀት ለቢሮው አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣የጽዳት እቃዎች ፣የጽ/መሳሪያ እቃዎች ፣የኮንስትሪክሽን እቃዎች እና የህትመት ሥራ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ አግባብ ያለው እና የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር / በመክፈል በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0- 18 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የእቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት የሚለየው የተጠቀሰውን ዝርዝር መግለጫ ያሟላ ሆኖ በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ሞልቶ ያቀረበ ነው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማሰራት ደረሰኙን ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ዋናውን ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዱ በፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0- 18 ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እሰከ ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ መሬት ቢሮ ቁጥር 0- 18 ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 3፡00 ታሸጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን በተመለከተ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዱ በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቀበሌ 08 ጋምቢ ጠቅላላ ሆስፒታል ጎን ቢሮ ቁጥር 0-18 ከተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአብክመ መሬት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 0-18 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 71 31 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአብክመ መሬት ቢሮ
ባህርዳር