ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
73

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን በ2017 በጀት ዓመት ከCIP- የካፒታል በጀት የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር ወይም የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ነው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ ተለይቶ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ/ንብ/አስ/ ቡድን ወይም ቢሮ ቁጥር 13 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ/ን/አስ ቡድን ክፍል በቢሮ ቁጥር 13 በ16ኛዉ ቀን 3፡00 ታሽጐ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዛወራል፡፡
  9. የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ አሸናፊ ለምትሆኑ ተጫራቾች ግዥው የሚፈጸመው መሥሪያ ቤቱ /ግዥ/ ፈጻሚው በሚያቀርበው ናሙና ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡
  10. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 13 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 61 24 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ማንኛዉም ህጋዊ ተጫራች የማይመለስ 1000 /አንድ ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  12. የመንገድ ዳር መብራት ጥገና እቃ ግዥ ወጭዎችን የሚሸፍነዉ አሸናፊ ተጫራች ይሆናል፡፡
  13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here