ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

ባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በበጀት አመቱ ከሚያስራቸው ፕሮጀክቶች መካከል 1. የአስፓልት ጥገና ሥራ ከአኮቴት እስከ አዲሱ ሚካኤል አስፓልት ድረስ ያለዉን የአስፓልት ጥገና ሥራ መሳተፍ ለሚልፈጉ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 2 እና በላይ የሆኑ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  2. ከላይ የተጠቀሰውን ፕሮጀክት ለማሰራት አስፈላጊውን ሁሉ የሰው ሃይል የማቴሪያል እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን የሚያሳይ በስማቸው የታሸገ የፋይናንሽያል እና የቴክኒካል የመወዳደሪያ ሃሳቦችን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 የማይመለስ ብር 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛት ምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የተጫራቹንና የኘሮጀክቱን ስም በግልጽ ተቀባይነት ባለው የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ1 ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ፡፡
  6. ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ዉ.ሁ1 ላይ በተገለዉ ቀን መሰረት ይሆናል፡፡
  7. ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ /ቴክኒካል/ እና ጨረታ ዋጋ /ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፓች ማህተም በማድረግ መታሸግ ይኖራባቸዋል፡፡ (አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ)፣
  8. ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ኮቢ-01/02 በቀን 15/09/2014 ዓም በተሻሻለዉ መመሪያ መሰረት የጨረታ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘዉን መመሪያ በደንብ ያንብቡት፡፡
  9. የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚቀርቡት ለመንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 22ኛ ቀን ሳጥኑ እስኪታሸግ ድረስ ሲሆን ጨረታው በይፋ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ22ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ 4፡00 ላይ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  10. ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በስልክ ቁጥር 058 320 18 78 /058 320 32 46 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  11. በባህር ዳር ከተማ ውስጥ በባለፈው አመት ውስጥ ፕሮጀክት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
  12. ማንኛውም ተጫራች ከሥራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ የሥራ አይነቶች ላይ የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ሥራውን እንዲሰራው ይገደዳል፡፡
  13. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ አሰሪ መሥሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም፡፡
  14. ማንኛውም ተጫራች በሚሞላው ሰነድ ላይ የሚፈጠር ሥርዝ ድልዝ ከውድድር ውጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ለግንባታ ሥራዎች ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ 2011 ዓ.ም መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ፡፡
  15. ተጫራቹ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ በቁጥር ቢያንስ 1 (አንድ) ማቅረብ አለበት፡፡
  16. የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here