የጨረታ ቁጥር
EEU/DMR/SC-PGS/NCB-04/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅኑ እና በስሩ ለሚገኙ ማዕከላት የሚያገለግሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዬ ዓይነት መስሪያ መሳሪያዎች ፣የተሸከርካሪዎች ቅባት ፣የመታወቂያ መስሪያ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የዕቃ ዓይነት | ብዛት | ሎት
|
የጨረታ ማስከበሪያ
(ሲፒኦ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) |
ጨረታዉ የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀን |
1 | የተለያዩ አይነት የተሸከርካሪዎች ቅባት እና ዘይት | ሎት 1 | 30000 (ሰላሳ ሽህ ብር) | ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ | |
2 | የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ | ሎት 2 | 25,000 /ሃያ አምስት ሽህ ብር/ | ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ | |
3 | የመታወቂያ መስሪያ ማሽን | ሎት 3 | 20,000 (ሀያ ሺህ ብር) | ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ | |
4 | Mechanical tool kit | 2 | ሎት 4 | 30,000 (ሰላሳ ሽህ ብር) | ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ |
5 | የኮንክሪት ምሰሶ መዉጫ ስታፌ | 90 | |||
6 | የእንጨት ምሰሶ መዉጫ ስታፌ | 40 | |||
7 | ተረቤላ ባለ 22(Auger Bit) | 50 | |||
8 | ተረቤላ ባለ 24( Auger Bit) | 21 | |||
9 | ተረቤላ ባለ 32( Auger Bit) | 2 |
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ፣የአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣የምዝገባ ምስክር ወረቀትና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ያላቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኢሌክትሪክ አገልግሎት ደብረ ማርቆስ ሪጅን ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 በመምጣት የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በካሽ በመክፈል ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም ድረስ የጨረታው ሰነድ መውስድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የመወዳደርያ ሰነዳቸውንና የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስከበሪያ በሎት በተገለፀው መሰረት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም 8፡00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ሚያዝያ 6/2017 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 እንቦሳ የገበያ ማዕከል ህንፃ አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኘዉ የሪጅኑ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል፡፡
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር (+25158 178 46 33) መደወል ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደብረማርቆስ ሪጅን