ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
74

በፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ለዲስትሪክት እና ለወረዳ አገልግሎት የሚዉል የጽህፈት መሳሪያ፣ የኮምፒተር ወረቀት፣ የብር ማሰሪያ ጎማ፣ ሰማያዊ እስክርቢቶ እስቴፕር ሽቦ ትንሹ ፣ማህተም ቀለምና ባህር መዝገብ ትልቁ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በየዘርፍ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. ከብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ ግዥ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን መረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ፣ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ሁለት በመቶ ከባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ከፖስታው ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡
  4. የእቃዎችን አይነት ዝርዝር መረጃ ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ በመ/ቤቱ ህጋዊ ደረሰኝ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጆዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማድርግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት 3ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በመጨረሻው ቀን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ 8፡00 ላይ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ጨረታው ሥርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታውን ዝርዝር መረጃ በፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 15 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የጽ/መሳሪያ እና የጽዳት እቃዎች ዝርዝር ስፔስፊኬሽን ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ

 

ተ.ቁ የእቃው አይነት መለኪያ ብዛት ስፔስፊኬሽን የአንዱ ዋጋ ጠ/ዋጋ
1 ሰማያዊ እስክርቢቶ ፓኬት 1475 የኬንያ ቢክ 1ኛ ደረጃ cristal    
2 የብር ማሰሪያ ጎማ በኪሎ 118 Light band Best quality    
3 ባህር መዝገብ ትልቅ በቁጥር 236 25*35 የውጭው    
4 እስቴፕለር ሽቦ ትንሹ ባኮ 295 Kangaro 24/6-1m    
5 ማህተም ቀለም በቁጥር 285 አንደኛ ደረጃ Horse    
6 የፕሪተር ቀለም ደስታ 740 Double A    

 

ፀደይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here