የጨረታ ቁጥር 008/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀና ኢነርጅ ቢሮ በመደበኛ እኛ በተለያዩ ፕሮጀክቶች የበጀት ምንጭ ሎት 1 water quality test kit instruments and reagents ሎት 2 የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 3 የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ሎት 4 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 5 ዋተር /ቦትል የውሃ ማጣሪያ/ ተወዳዳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት እቃ ሁለት በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
- ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን 8፡00 ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 በ8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መዝጊያ ቀን 16ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 78 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የአብክመ ውሀና ኢነርጅ ቢሮ