ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
62

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2017 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርቴፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የወጣው ጨረታ ከ200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ማንኛውም ግዥ ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ ሁለት በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  5. ዝርዝር መግለጫውን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ብር 3,000 (ሶስት ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  8. የጨረታ አሸናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ተገቢውን የውል ማስከበሪያ ከባንኮች በተረጋገጠ የጠቅላላ ግዥ ዋጋ አስር በመቶ ሲፒኦ በማቅረብ ውል መያዝ አለበት፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በአንድ በታሸገ ፖስታ በደ/ማርቆስ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛ ቀን 3፡00 ድረስ ማስገባት  አለባቸው፡፡ ጨረታው የሚከፈተው  በዚሁ ቀን  ከጠዋቱ 3፡30  ሲሆን  ተጫራቾች  በተገኙበት /በተወካይ ፊት ይሆናል፡፡
  10. ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. አድራሻ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ ቁጥር 09 20 50 43 80 /09 20 5068 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here