ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
69

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን በ2017 በጀት አመት አገልግሎት ለሚሰጣቸው ሴ/መ/ቤቶች ማለትም

ሎት 1 የስፖርት ቁሳቁሶችን ለስፖርት ጽ/ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  3. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  4. የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያለው፡፡
  5. የግዥዉ መጠን ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ  የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  6. የእቃዉን አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማንኛውም ተጫራች የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/  በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ጎ/ቆ/ወ/ፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት የግዥዉ ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊ ድርጅቱ አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ የዉል ማስከበሪያ የጠቅላላዉን ዋጋ አስር በመቶ በሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጎ/ቆ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር  03 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ29/07/17 እስከ 14/08/17 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በቀን 14/08/17 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታውን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት ጎ/ቆ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 በቀን 14/08/17 ዓ.ም ከጠዋቱ በ3፡30 ይከፈታል፡፡
  11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ጎ/ቆ/ወ/ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 058 556 75 58 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. በጨረታው ሰነዱ ላይ ሥርዝ ድልዝ በሌለበት ሁኔታ መሞላት አለበት፡፡ ሆኖም ሥርዝ ድልዝ ካለ  ፓራፍ  መደረግ አለበት፡፡
  14. መ/ቤቱ ሃያ በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል እና ማንኛውም ተጫራች ግዥ/ንብ/አስ/ቡድን ሳምፕል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  15. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላው ሲሆን እቃውን ጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ ያቀርባል፡፡
  16. ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡

የጎንጅ ቆለላ ወረዳ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here