ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
107

በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የወገዳ ከተማ አስተዳደር ከ/መ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የዲችና ካልበርት ግንባታ ለማሰራት ማንኛዉንም አቅርቦት በተጫራቹ የሚቀርብ መሆኑን እየገለፅን ሎት 01 ከወገዳ ከተማ መነሀሪያ ጀርባ ከነባሩ ኮብል ጀምሮ እስከ መድሀኒአለም ቤተከርስቲያን መዉጫ 20 ሜትር መንገድ የዲች ርዝመት 315 ሜትር እና ሎት 02 መድሀኒአለም ቤተከርስቲያን መዉጫ 20 ሜትር መንገድ እስከ ጎንደር በር ፓርክ ሲሆን የዲች ርዝመት 295 ሜትር በግልጽ  ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን  መለየት  ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ /ወቅታዊ/ የዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ማስረጃዉን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ መሆኑን የሚረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በሰነዱ ላይ የሞሉት አጠቃላይ ዋጋ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸዉን ለእያንዳቸዉ 100 /አንድ መቶ ብር/ የማይመለስ ገንዘብ በመክፈል የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ዘወትር በሥራ ሰዓት ሰነዱን መዉሰድ ይቻላል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን እና ሌሎች መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት በወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት የግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው በ22ተኛው ቀን በዚሁ እለት በ3፡30 ታሽጎ 4፡00  ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተቀመጠው ስዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባይኖሩም ለመክፈት አያስተጓጉሉም፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ሥራ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ ብር ድምር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ዋስትና ወይም በመ/ቤቱ ደረሰኝ በመሂ-1 በመቁረጥ ኮፒ አድርገዉ በጨረታ ፖስታዉ ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊነታቸዉ እንደተገለፀላቸዉ  የዉል ማስከበሪያ አስር በመቶ በመ/ቤቱ  ደረሰኝ ወይም በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ ማንኛውንም ወጭ ያጠቃለለ መሆን ይኖርበታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከመወዳደሪያ ሃሳቡ ላይ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን ፣ሙሉ አድራሻቸውንና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
  9. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እና በጨረታ እራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡ ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እና ለወደፊቱም ከመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልጻን፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  11. ተጫራቾች ለመወዳደር Gc ወይም Rc የግንባታ ፈቃድ ያላቸዉ መሆን አለበት፡፡
  12. ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉት ከደረጃ 8 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸዉ ናቸው ፡፡
  13. ደረጃ 8 እና በላይ የግንባታ ፈቃድ ያላቸዉ በጥቃቅን የተደራጁ ወጣት ተጫራቾች የልዩ አስተያየት ተጠቃሚ የሚያደርጋቸዉ ወቅታዊ የሆነ የድጋፍ ደብዳቤ ለጽ/ቤቱ በአድራሻ የተጻፈ ማስረጃ ማያያዝ አለባቸዉ፡፡ ነገር ግን ጨረታዉን የሚያሸንፉ ከሆነ ካርታ እና ፕላን ማስያዝ አለባቸዉ፡፡ እንዲሁም ተጫራቾች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  14. አንድ ተጫራች ከአንድ በላይ ሰነድ መግዛት እና ከአንድ ፕሮጀክት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
  15. የጨረታዉን /የስራ/ ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  16. መ/ቤቱ ከጨረታ አሸናፊው የሚፈለገውን አገልግሎት ጥራቱን ሳይቀይር በመመሪያዉ መሰረት ሊጨምር /ሊቀንስ/ ይችላል፡፡ ለበለጠ ማብራሪያ ወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 058 667 04 03 እና የግ/ፋ/ንብ/አስ/ቡድን 058 667 03 89 እንዲሁም በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
  17. በጨረታዉ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ሞልተዉ አሸናፊ ሆነዉ የሚመረጡ የግንባታ ተቋራጮች ዉል ይዘዉ ወደ ስራ ሲገቡ የቅድሚያ ክፍያ አይፈቀድላቸዉም፡፡ እንዲሁም በአ/ብ/ክ/መ/ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

የወገዳ ከተማ አስተዳደር ገ/ኢ/ል/ት/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here