በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሳንጃ ሆስፒታል ለ2017 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ሎት 01 የጽህፈት መሳሪያ ፣ሎት 02 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 03 አልባሳት ፣ሎት 04 የመኪና ጎማ ፣ሎት 05 የቧንቧ እቃ ፣ሎት 06 የኤሌክትሪክ እቃ እና ሎት 07 የህንፃ መሳሪያ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- ዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለካታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50 /ሰላሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት በሳንጃ ሆስፒታል ግ/ፋ/ ቢሮ መግዛት ወይም ማግኝት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው ወይም በጥሪው ማስያዝ ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ ለየብቻ በመለየት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ29/7/2017 ዓ.ም አስከ 13/08/2017 ቀን ጀምሮ መውሰድና መመለስ የሚችሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ማለትም በ14/08/2017 ከጠዋቱ 2፡00 ታሽጎ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤታችን ሳንጃ ሆስፒታል የስብሰባ አዳራሽ በግልጽ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው የሚለየው በሎቱ በጥቅል እቃ ዋጋ ሲሆን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በነጠላ ዋጋ አሸናፊ የመለየት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናው ድርጅት ማዕከላዊ ጎንደር ታች አርማ ወረዳ ዓ/ህግ ጽ/ቤት ቀርቦ ውል መውሰድ የሚችልና እቃዎችን ሳንጃ ሆስፒታል ባለው የንብረት መጋዝን በዝርዝር ማስረክብ የሚችል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 18 19 85 88 ወይም 09 39 24 50 07 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊው እቃውን ማቅረብ ያለበት በጨረታ ሰነዱ ላይ የተሰጠውን ሞዴል እንጅ ሥርዝ /ድልዝ ሌላ ተመሳሳይ እቃ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ከጨረታ ሰነዱ ላይ ከተቀመጠው የዋጋ ሞሙያ ፎርም በስተቀር በማሰባሰቢያ ሚሞሉ የዋጋና የሞዴል መረጃን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን አስር በመቶ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት መሥሪያ ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
- ከጨረታ ውጭ ሊያደርጉ የሚችሉ ሁኔታዎች የሚከተሉት ጥፋቶችና ምክኒያቶች አንዱን የፈፀመ ተጫራች መ/ቤቱ ከጨረታ ውጭ ሊያደርገው ይችላል፡፡
- በአዋጅ የተቀመጡ ድንጋጌዎች እና ይሂን አዋጅ ለማስፈፀም የወጣውን መመሪያ ሊጥስ ወይም በጨረታ ሰነዱ የተመለከቱትን መሰረታዊ ጉዳዩች ሳያሟላ ሲቀር፡፡
- ቀደም ሲል በወረዳው በወጡ ጨረታዎች የተለየ አስተያየትን ለመግኘት ወይም ጨረታውን ለማሸነፍ ለማንኛውም ባለስልጣን ወይም ሰራተኛ መደለያ የመስጠት ሃሳብ /ማቅረቡ በአሳማኝ ሁኔታ ሲታወቅ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማጭበርበር ተግባር መፍፀም ወይም ከሌላ ተወዳዳሪ ጋር መመሳጠር በአሳማኝ ሁኔታ የተረጋገጠ ከሆነ፡፡
- ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በጨረታ ሳጥኑ ካስገባ (ከሰጠ) በኋላ እራሱን ከውድድሩ ለማግለል ከፈለገ እና ጨረታው ከመታሸጉ በፊት የማግለል አሳቡን በጨረታ ሰጥን ያስገባ ከሆነ፡፡
- ተጫራቾች የህግ ፣አዋጅና የዚህን መመሪያ አንቀዖች በጨረታ ሰነዱ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ያላከበር ከሆነ፡፡
- ካሁን በፊት በተሳተፈበት የመንግስት ጨረታ የገባውን ግዴታ ያልፈፀመ ከሆነ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ እንዲያስይዝ የተጠየቀውን ያላስያዘ፡፡
- የጨረታውን ሂደት ለማዛባት የሞከር፡፡
- የሞላው ዋጋ ሥርዝ ድልዝ ሆኖ ለማንበብ አስቸጋሪ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
- ሁሉንም አይነት የተዘረዘሩትን እቃ ዋጋ በጥቅል ወይም በሎት ያልሞላ ከሆነ፡፡
ለበለጠ መረጃ 09 18 19 85 88 /09 39 84 50 07 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሳንጃ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል