ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2017

የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በከተማ ውስጥ የሚያሰራቸውን ኮብል ንጣፍ ስራ ሎት1. ቀበሌ01 እና 02 ቀበሌ መካከል አንከሻ መሰናዶ ትምህርት ቤት እስከ ቢያድጎ ቆለጭ ቤት 260 ሜትር ሎት1. በGCእና RC በደረጃ 7 እና በላይ ፈቃድ ካላቸው ተጫራቾች መካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል ፡፡

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢነት/ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የታደሰ የግንባታ ፈቃድ ማረጋገጫ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ዋና እና ቅጂ በማድረግ ከመጫረቻ ሠነዱ ጋር አያይዞ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ሲሞላ ያለምንም ስርዝ ድልዝ መሞላት አለበት፡፡
  6. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀን ነው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስታዎቂያው ከወጣበት ቀን 6/08/2017 ዓ.ም ጀምሮ በወጣው ግልፅ ጨረታ ለ21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 / ሦስት መቶ ብር/ በመግዛት የጨረታ ሰነዱን ግዥ ፋይ /ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት እስከ 30/08/2017 ዓም 3፡00 ማስገባት ይችላሉ፡፡
  10. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግዥፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 በቀን 01/09/2017 ዓ.ም 3፡00 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የህዝብ በአል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1 ብር 42,000 /አርባ ሁለት ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ የሚችሉ እና በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ጥቃቅን ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  12. የሁሉም የግንባታ ዓይነቶች ዝርዝር መግለጫ እና ለእቃዋች ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  13. ከተዘጋጀው የመሀንዲስ የዋጋ ግምት አንፃር የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ከ25በመቶ ዝቅ ብሎ በመግባቱ ታጫረቹ በተፈለገው ጥራትና ጊዜ ማከናወን አይችልም ብሎ አሰሪ መ/ቤቱ ሲያምን በጨረታው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበ ድርጅት ወይም ተቋራጩ ዝርዝር የግንባታ ዋጋ እና የግንባታ መረሃ-ግብር እንዲሁም ባቀረበው የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ መሰራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ አሸናፊነት በተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ የማቅረብ ግዴታ ያለበት ሲሆን ፤ይህን ማድረግ ካልቻለ ከውድድር ውጭ ሆኖ ሁለተኛ የወጣው ተጫራች የሞለው ዋጋ ከወቅቱ የገበያ ዋጋ ጋር ሲነጸጸር የተሻለ ሆኖ ከተገኘ ስራው ለዚህ ተወደዳሪ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  14. የግንባታ ግዥ ከማህንዲስ ግምት በላይ እስከ 10 በመቶ ድረስ ከሆነ አሰሪው መ/ቤት ካላመነበት ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. የጨረታው አሸናፊ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት፡፡ እንዲሁም  በጥቃቅን የተደራጁ ከሆነ ስራና ስልጠና ጽ/ቤት የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ የኖርባቸዋል፡፡
  16. አሸናፊው ድርጅት የሚሰራቸውን የኮብል ስራዎች ለሎት 1 የኮብል ድንጋይ ጽ/ቤቱ የሚችል ሆኖ ኮብል ድንጋዩን መጫን ማጓጓዝ ከሳይት የተረፈውን መመለስ የግንባታ ተቋራጩ ይሆናል፤ እንዲሁም ሌሎችን ማንኛውንም ማቴሪያሎች ወጭ በራሱ አቅርቦ መስራት የሚችል መሆን አለበት፡፡
  17. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  18. ተወደዳሪ ኮንትራክተሮች ከአሁን በፊት አንድ እና ከዚያ በላይ ለተሰሩ ስራዎች የመልካም ስራ አፈፃፀም ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  19. የውድድሩ ሁኔታ በሎት ዋጋ ሲሆን በተጨማሪ በአብክመ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
  20. ተጫራቾች በሌለ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት የተከለከለ ነው፡፡
  21. የውል ማስከበሪያው ዋስትና ፀንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 / ሰላሳ/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  22. አሸናፊው ድርጅት ቅድመ ክፍያ መውሰድ የሚችለው ለሚወስደው ቅድመ ክፍያ ተመጣጣኝ የሆነ መያዣ ወይም ኮላተራል ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  23. ለተጨማሪ መረጃ የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ፋይ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 02 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582240724 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡

የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አስተዳዳር ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here