በአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በ2017 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለToyota Pickup Hilux revo, model-GUN 125L-DNFXHN ለሆነች መኪና፤ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው ፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው ነገር ግን ከላይ ከ 1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት በባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 11 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሚያዚያ 06 እስከ ሚያዚያ 20 /2017 ዓ.ም ማስገባት አለባቸው፡፡ ጫረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀን በአየር ላይ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ሚያዚያ 21/ 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባህርዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 11 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0908649967 በመደወል ማግኘት ይችላል፡፡
የምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት