በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ማካይኝነት የምስ/ደ/ወ/ አስተዳደር /ጽ/ቤት ለቢሮ ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የግንባታ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉና ተጨማሪ እሌት ታክስ / ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሻተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ 300 ብር በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፡
- የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትፈልጉ ከ6/8/.2017 ዓ.ም ጀምሮ በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ዘወትር በሥራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የግንባታ ማቴሪያል ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊዉ የሚለየዉ በሎት ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በምስራቅ ደምቢያ ወረዳ ገንዘበ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 ከ6/8/2017 ዓ.ም እስከ ባሉት ተከታታይ ቀናት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ /ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 1በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በፖስታዉ ታሽጎ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ ፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ20/8/2017 ዓ/ም በ3፡30 ታሽጎ በግዥ ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 6 በዚሁ ቀን በ4.00 ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባይገኙም ለጨረታዉ መሟለት የሚገባቸዉ ሁኔታዎች ከተሟሉ ተጫራቾች በሌሉበት ጽ/ቤቱ ጨረታዉ ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
- ተጫራቾች በጨረታዉ ማሸነፋቸዉ እና የዉል ስምምነት እንዲፈጽሙ በተገለጸበት ጊዜ ከአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ10በመቶ የዉል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ / ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ደረሰኝ ማስያዝ እና ንብረቱን ምስ/ደ/ወ/አሰተዳደር ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግና የጫኝና አዉራጅ በተጫራቹ የሚሸፈን መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በጨረታዉ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0583350601 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት በየትኛዉም ደረጃ በነበራቸዉ የአፈጻጸም ችግር ምክንያት ታገዱ የታገዱ አቅራቢዎችን አይመለክተው ፡፡
የምስራቅ ደምቢያ ወረዳ አስተዳደር ጽ/ቤት