ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

ቁጥር 07/2017

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን /አሚኮ/  ሎት 1. የአይሲቲ ዕቃዎች ፣ሎት 2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን  በድጋሚ  ሎት 3. የኤሌክትሮ መካኒካል ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ አሸናፊዉን በመለየት መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ በጨረታዉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ፤የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ፎቶ ኮፒ አድርገው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  2. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጠቅላላ ድምር ዋጋ 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ድረስ 300 /ሶስት መቶ/ ብር በመግዛት  አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 104  መዉሰድ  ይቻላል፡፡ ለሎት እና ሎት2 .  የቴክኒክ እና የፋይናንስ ሰነዶችን ለየብቻ በመሙላት የራሳቸዉን ቴክኒክ ሰነዶችን በማዘጋጀት በሁለት ኮፒ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት ለዚህ ሲባል በተዘጋጀዉ የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛዉ ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ ፤ሎት 3.የፋይናንስ  ሰነዶችን በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ  በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸዉ፡፡ በቴክኒክ ምዘና 70 እና በላይ ነጥብ ያመጡ ድርጅቶች ወደ ፋይናንስ ዉድድር የሚቀርቡ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ይዘጋና በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ግዥና ንብረት ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው በእለቱ ይከፈታል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1 በመቶ በባንክ የተመሰከረለት ቼክ/ስፒኦ/፣በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ይህም ሲባል በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ከጨረታው የፋይናንስ ሰነድ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 4፡00 ይዘጋና 4፡30 ይከፈታል፡፡
  7. ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚፈለጉት የአይሲቲ ፣ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሮ መካኒክ ዕቃዎች ዓይነት፣ ብዛትና ስፔስፍኬሽን እንዲሁም የውል ቃሎች ከሰነዱ ጋር ተዘጋጅቶ የቀረበ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  9. የጨረታ ሰነዱን አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ቀበሌ 13 አየር መንገድ ከሚወስደዉ አስፓልት ገጠር መንገድ ከፍ ብሎ ባለዉ ህንጻ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 ድረስ በመምጣት መዉሰድ ይቻላል፡፡
  10. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 320 97 35 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here