የፍኖተሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት በተለያዩ ሞተር ቤቶች እና በግቢዉ ዉስጥ የሚገኙትን አገልግሎት የሰጡ እና ያልሰጡ እቃዎችን ሎት1. ዲሲ አይ ቧንቧ ፣ሎት2. ዲሲ አይ መገጣጠሚያና ሲአይ መገጣጠሚያ፣ ሎት3.ኤች ዲፒ መገጣጠሚያ ፣ሎት4. ለፓምፕ የሚያገለግል የሰራ እና ያልሰራ ኬብል ፣ሎት5. የቧንቧ መፍቻዎችና የስራ መሳሪያዎች፣ ሎት6. የመኪና እቃዎች ፣ሎት 7. የመኪና ጎማ ፣ሎት8.አሮጌ ቧንቧ፣ ሎት9. አገልግሎት የሠጡ ፓምፕ ዕቃዎች ፣ሎት10. አገልግሎት የሠጡ ካልኩሌተሮች፣ ፓወርሴቨር፣ ቆጣሪ ቦዲዎች፣መገጣጠሚያዎች ፣ስብርባሪ ብረታ ብረቶች እና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች ፣ሎት11.ተወዝዋዥ ፓምፕ ባሉበት ሁኔታ በጨራታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- ለጨረታ የቀረበዉን ንብረት በራሱ ወጭ አዘጋጅቶና ጭኖ መግዛት/ማንሳት የሚችል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፓስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር /4/ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ስዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ ፓስታዉ ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 ቀናት ማንሳት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ታትሞ ይቆያል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል፣ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀናት በተመሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200/ ሁለት መቶ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ስዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ብር አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊዉ ያሸነፈበትን ገንዘብ እንደከፈለ ንብረቱን ይረከባል፡፡
- አሸናፊው የሚለየዉ ከፍተኛ ዋጋ የሞላ ይሆናል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ/በከፊል/የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡
- ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ /ሎት /በማድረግ ሲሆን ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ:: ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ0587751387/0923426123 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት