በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የአምባጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ/ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት በከ/መ/ል/ጽ/ቤት ስም ለሚያሰራው የጠጠር መንገድ ስራ 1ኛ የማሽን ኪራይ ማለትም ሮሎ እና ሎደር የመሳሰሉ 2ኛ ጥራቱን የጠበቀ ጋራጋንቲ እራሱ አምርቶ በቢያጆ በሲኖትራክ ገብርኤል ሰፈር እና ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ አካባቢ ድረስ ማቅረብ የሚችል /የሚደፋ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በየዘርፍ የዘመኑ የታደስ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግዥ መጠኑ ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ /ብር እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለማሸነፍ ከላይ ከቁ/1-3/ የተጠቀሱትን የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) እና ናሙና የሚያስፈልጋቸው ከጨረታ ሰነዱማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200.00/ሁለት መቶ/ብር በመክፈል ከአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤትቢሮ ቁጥር 05 ዘወትር በስራ ስዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ስርዝ ድልዝ ከሆነ ሰነዱ ተቀባይነት የለውም ወይም መፈረም አለበት፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የሚለየው በሎት ወይም በተናጠል በየሎት ምድባቸው የሚለይ ይሆናል ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፋያ ትዕዛዝ (ሲፒዩ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- በጨረታ 1ኛ የወጣውን ውል እስከሚወስዱ ድረስ 2ኛየወጣው የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስለትም ፡፡
- አሸናፊው አሸናፊነቱን ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ውል መውሰድ አለበት፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ማለትም ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በአ/ጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ /ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት 13 /8/2017ዓ.ም እስከ 27/8/2017 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ጨረታውን መግዛት ይችላሉ ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 13/8/2017 እስከ ሚያዚያ 28/2017 ዓ.ም በተዘጋጀው ሳጥን ከጥዋቱ 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታው ከመክፈት አያግደውም ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ የሚቀጥለው ቀን ይሆናል ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአምባ ጊዮርጊስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር0581180846/ 0935284602 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአምባጊዮርስ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት