ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
84

የጨረታ ቁጥር 009/2017

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሃ እና ኢነርጅ እና በማዕድን ሀብት ልማት  ቢሮ  በመደበኛና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በተገኘ በጀት ሎት ሎት 1 ፡- የጅኦሎጅ እቃዎች ,ሎት 2 ፡- የከበሩ ድንጋይ ማስዋቢያ እና ማስቀመጫ እቃዎች፣ሎት 3፡- የኤሌክትሮ መካኒካል መፍቻዎች /ቱልስ ኪት / ተወዳዳሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት  ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡-

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ያላቸው እና የግዥው መጠን ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. ተጫራቶች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. የእቃው  ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ  ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የውሀ እና ኢነርጅ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  6. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ /CPO/ ለሎት1፡- 50,000፣ለሎት 2 ፡- 300,000 ለሎት 3 ፡-30,000ለሎት 4 እና 5፡- 20,000  ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በውሀ እና ኢነርጅ ቢሮ ቁጥር 27 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የመቁጠሪያ ቀናት ለተጫራቾች ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  9. ተጫራቾች የመጨረቻ ሰነዶቻቸውን በመሙላት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 16ኛው ቀን00 ሠዓት ከመድረሱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ጨረታው በዚሁ ቀን 8.00 ሠዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 27 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መዝጊያ ቀን /16ኛው ቀን/ በዓል ቀን ከሆነ በተመሳሳይ ሠዓት በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ሌሎች ተጫራቶች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  12. ቢሮው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. ተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር ዐ58-22-2ዐ1-32/ዐ58-22ዐ-10-78/ በመደወል መጠየቅ ይችላል፡፡

የአብክመ የውሃ እና ኢነርጅ እና በማዕድን ሀብት ልማት  ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here