ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
90

የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ ሎት1- የተለያየ መጠን ያላቸው BUITWELDING HDPE PIPE ሎት 2- Flanged Water Meter, DN 100 mm, CI, PN16, Flanged Bulk Ultrasonic Water Meter With Counter 2 Internal Threaded Flanged 150 ሎት 3- እስቴሽነሪ (የጽህፈት መሳሪያ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ /የታደሰ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግዥው መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሽህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 210 የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት ኦርጅናል፣ ኮፒውን ፋይናሻል ሰነዱን እና የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነዱ ጋር ለየብቻ በማሸግና ሁሉንም በአንድ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በዋናው ቢሮ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2በመቶ በባንክ በተመሰከረለት CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /un Conditional Bank Garanty ከቴክኒካል ጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው፡፡
  7. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00  ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  8. አሸናፊዎች አሸናፊነታቸው ከተለየበት ቀን ጀምሮ ከ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ጽ/ቤቱ በመቅረብ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና ውል በመፈፀም እቃውን ባ/ዳር ከተማ ውሃ አገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማቅረብ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 05 83 20 5ዐ 79 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ አድራሻ ቀበሌ 08 ዋናው የባህርዳር ከተማ የመ/ወው/ፍ/አገ/ድርጅት
    የባህር ዳር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here