በምስ/ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳና የደብረ ኤሊያስ ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ለ2017 በጀት ዓመት ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያ ፤ሎት 2 ቋሚ እቃዎች ኮምፒዉተር እና ተዛማች እቃዎች ፤ሎት 3 የጽዳት እቃዎች ፤ሎት 4 የህትመት ዉጤቶች ሎት 5 ኤሌክትሪክና ተዛማች እቃዎችን ሎት 6 የህንጻ መሳሪያዎች ሎት 7 የዉጭ ፈርኒቸር ሎት 8 የአገር ዉስጥ ፈርኒቸር ሎት 9 ፎቶ ኮፒ ማሽንና ኮምፒዉተርና ተዛማች እቃዎች ጥገና ፤ሎት 10 የአገር ዉስጥ ፈርኒቸር ጥገና ፤የበር፣ የመስኮት፣ የጠረጵዛ እና የሽልፍ ቁልፍ ጥገና ህጋዊ ከሆኑ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉተን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በ2017 ዓ/ም በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ፣
- የግዥ መጠን ከ200,000 ሺህ ብር እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፣ኮምፒዉተርና ተዛማች እቃዎች ከ200,000 ሺህ ብር በታችም ጠቅላላ ዋጋ ቢሆን የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት አብሮ ተያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳታፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፣
- ለሚገዙት እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ/እስፔስፍኬሽን/ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 20/ ሃያ ብር /በመክፈል ከሎት 1 እስከ ሎት 10 ድረስ የጨረታ ሰነዱን የ2ቱንም ወረዳ ፍ/ቤቶች ከጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ገንዘብ ያዥ መውሰድ ይችላሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት 1% ከ1-10 ላሉት ሎቶች በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፣
- ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት 11፡00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ሰነድ መግዛት ይችላል፣
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማደረግ የደብረኤልያስ ወ/ፍ/ቤት እና የማቻከል ወረዳዎች ፣ ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ለእያንዳንዱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እስከ 2፡59 (ሁለት ስዓት ከሃምሳ ዘጠኝ ደቂቃ) ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል 3፡00 ሲሆን የጫረታ ሳጥኑ ተጫራቾች በተገኙበት ይታሸጋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የ2ቱም ወረዳዎች ጎዛምን ወረዳ ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ በ16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ጀምሮ የሚከፈት ሲሆን ሆኖም ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ፖስታው መከፈቱ የማይስተጓጎል መሆኑን እንገልፃለን፣
- የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀን በአል ከሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፣
- የጨረታ አሸናፊ መሆን የሚቻለው በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ ዝቅተኛ ያቀረበ ተጫራች መሆኑ ታውቆ የሁሉም እቃዎች ዋጋ መሙላት ይኖርበታል፣ እና በዋጋ በመሙያዉ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ስም ፤ፊርማ እና ማህተም መደረግ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ ከተዘረዘረው ግዥ መጠን 20 በመቶ ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል፣
- አሸናፊው ከጠቅላላ ዋጋው ውስጥ 10በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅበታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ወ/ፍ/ቤት የአነደድ ፣ወ/ፍ/ቤት ምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አጓጉዞ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቹ በጨረታው ለመወዳደር ላወጣው ወጭ መ/ቤቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፣ የመጫረቻ ሰነድ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ፀንቶ ይቆያል፣
- አሸናፊዉ ድርጅት በስሙ የታተመ ተከታታይ ቁጥር ያለዉ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0587713129 በመደወል መረዳት ይቻላል፡፡
የደብረ ኤሊያስ ወረዳ ፍ/ቤት