ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
176

በምስራቅ ጎጃም ዞን የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ንብ/ አስ /ቡድን በሁ/እ/እ/ወ/ አስተዳዳር ጽ/ቤት  G+4 ህንጻ ተሰርቶ የተጠናቀቀ  ቢሆንም አሁን ላይ ባለው ሁኔታ የጣራና ልዩ ልዩ ቦታዎች ላይ ስለሚያፈስና የጥገና ስራ ስላስፈለገው ሙሉ የጥገና ወጪውን ተጫራቾች ችለው ማሰራት ይፈልጋል፡፡ እንዲሁም ለሁ/እ/እ/ወ/ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የጽ/መሣሪያ ፣ የጽዳት እቃዎች እና በወረዳው ውስጥ ላሉ ሴክተሮች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስገንባት/ ለመግዛት ይፈልጋል ፡፡  ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማቅረብ የሚችሉ ፡፡
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት  የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1 – 3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጨረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ፡
  5. የጨረታ ሰነዱ ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለጽ/መሣሪያ ብር 300/ ሶስት መቶ ብር/ ለጽዳት እቃዎች ብር 150/ አንድ መቶ አምሣ/ ብር ለግንባታው ጥገናው ብር 300/ ሶሶት መቶ ብር / ለባቱማ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 100/ አንድ መቶ ብር ከሁ/እ/እ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ከረዳት ገ/ያዥ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት የሞሉትን ጥቅል ዋጋ የጽ/መሣሪያ 70‚000/ሰባ ሽህ/ ብር ፣የጽዳት እቃዎች 60‚000 /ስልሣ ሽህ ብር/ ፣የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 20,000/ ሀያ  ሽህ/ ብር ፣ የግንባታው ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ 200,000/ ሁለት መቶ ሽህ ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲፒዮ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው በጥሬ ገንዘብ የሚያስዙ ከሆነ በሁ/እ/እ/ወ ገንዘብ ጽ/ቤት የገቢ ደረሰኝ መደረግ አና ደረሰኙ ከጫራታ ሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት፡፡
  8. አሸናፊው ተጫራች የውል ስምምነት እንዲፈፀም በተገለፀበት ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት የዕቃ/አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የግዥ ውል ማስከበሪያ ፕሮፎርማንስ ቦንድ በታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ትዕዘዝ /ሲፒኦ/ ወይንም በጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank grante/ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከአሸናፊው የሚቀርበው የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ መቆያ ጊዜ ውሉ ከሚጠናቀቅበት የመጨረሻ ቀን በኋላ ቢያንስ ለተጨማሪ 30 /ሰላሣ/ ቀናት ጸንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
  9. አሸናፊ ግንባታውን ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 25% ከማህንዲሱ ግምት ዝቅ ብሎ ካሞላ
  • Cost breakdown እና projeket work schedule እንዲሁም በሞላው ዝቅተኛ ዋጋ መስራት የሚችል መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ/conformation letter/አሸናፊነት ከተገለጸ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት የተጋነነ ዝቅተኛ ሞልተው አሸናፊ ሆነው የግንባታ ተቋራጭ ውል ይዘው ወደ ስራ ሲገቡ ቅድመ ክፍያ አይፈቀድላቸውም፡፡
  • የውል ማስከበሪያ የሞላውን ጠቅላላ ዋጋ 10በመቶ የነበረው ተሸሽሎ 25በመቶ የውል ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ግዴታ ይሆናል ፡፡
  1. የግንባታ የሂሳብ ስሌት በተመለከተ/አርቴሜቲክ ቸክ/ በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያስተካከለው ውጭ በተጫራቾች በሚቀርበው የመጫራቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና በጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  2. ለግንባታ ለፋይናስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች ቢያንስ 3 እና በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ ከሂሳብ ስሌት /አርቴሚቲክ ቸክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5 በመቶ ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ ተጫራቹ ከ3 በታች ከሆነ በጫራታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት/አርቴሜቲክ ቸክ/ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1በመቶ ድረስ ብቻ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡
  3. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት ኦርጅናል ለብቻው ቅጅውን ለብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ሁ/እ/እ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ግዥ ቡድን  ወይም ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓትጋዜጣው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለግንባታ ስራዎች ለ21 ተከታታይ ቀናት እስከ  22ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ ፡፡ ለሌሎች ግዥዎች ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ ከ16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ተጫራቾች የጫራታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ዋና እና ቅጅ ወይም ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ለመ/ቤቱ እና ለተጫራቾች ድህንነት እንጀ እንደ መወዳደሪያ መስፈርት አይሆንም፡፡
  4. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል በቢሮ ቁጥር 4 የጨረታ ጋዜጣው በወጣበት 22ኛው ቀን 3፡30 ታሽጐ በ4፡00 ይከፈታል ሌሎች ግዥዎች በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል ፡፡ የስራ ቀናት ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተጠቀሰው የጨረታ መክፈቻ ስዓት ባይገኙ መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው፡፡
  5. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  6. ውድድሩ በሎት ስለሆነ በአንድ ሎት የተቀመጡትን ዝርዝር ሙሉ በሙሉ መሙላ አለባቸው፡፡
  7. በጨረታው መሳተፍ ሚፈልጉ ስለጨራታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ ወይም በስልክ ቁጥር 0586610005 ወይም 0586611935 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. የእቃ ግዥዎች መ/ቤቱ ሚገዛውን እቃ 20በመቶ የመጨመር ወይም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  9. አሸናፊ ያሸነፈባቸውን እቃዎች በአሸነፋቸው ድርጅት በራሱ ወጭ መ/ቤቱ ከሚፈልግበት ቦታ ድረስ ማድረስ የሚችል መሆን አለበት የግንባታ ስራ እቃዎችን እራሱ ችሎ ግንባታውን እስከ ሚካሄድበት ቦታ ድረስ አቅርበው መስራት አለባቸው፡፡
  10. ተጫራቾች ለእቃ አቅርቦት ግዥዎችን አሸናፊው ውል ይዞ እቃውን የሚያቀርበት ጊዜ በ15 ተከታታይ ቀናት ማቅረብ የሚችል ለግንባታው በ20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ሰርቶ ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡ የጨረታ ሰነዱ 60 ተከታታይ ቀናት ጽንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  11. ለግንባታው ስራ በጨረታው የሚሳተፍ ተጫራቾች ደረጃ 7 GC ወይም BC እና ከዚያ በላይ መሆን  አለባቸው፡፡ በተጨማሪ በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽሎ በቀረበው በግዥ አፈጻጸም መመሪያ ቁጥር 1/2003  መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

የሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here