ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
70

የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ በ2017 በጀት ዓመት ዓመታዊ ውል በመያዝ ለተኝቶ ህክምና ታካሚዎች እና ካፌ አገልግሎት የሚዉል ሎት 1 የበሰለ ምግብ አቅርቦት በሆቴሎችና ካፍቴሪያ ዘርፍ ፈቃድ ላላቸው ግለሰቦች በግልጽ ጨረታ አውጥቶ ማስቀረብ እና የሆስፒታሉን ካፍቴሪያ በብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ ማከራየት ይፈልጋል፡፡ በካፌው የሚቀርቡ አገልግሎቶች፡- 1. የምግብ አይነት የተለያዩ ምግብ አይነቶችን ፣2. የተለያዩ አይነት ትኩስ መጠጦች የጀበና ቡናን ጨምሮ ፣3. የተለያዩ አይነት ቀዝቃዛ መጠጦችን ከአልኮል ወጭ እና መቀመጫ ወንበር ፣ 4. ጠረጴዛ ማቅረብ የሚችል እና 5 የሻይ ማሽን ፍራጅ ቴሌቪዥን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን አሸናፊ ተጫራች ያቀርባል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
  2. የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ፡፡
  3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. የሚቀርቡ የምግብ እና የመጠጥ አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ፋ/ንብ/አስ/ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቡሬ ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በተዘጋጀዉ ሳጥን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 2፡59 ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  9. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉን በተገኙበት በቡሬ የመ/ ደ/ሆስፒታል ውስጥ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በግ/ፋ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጎ 3፡30 በይፋ ይከፈታል፡፡ ቀኑ በዓል ወይም እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚቀጥሉት 5 የሥራ ቀናት በ5 ተከታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
  11. ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ እና በላይ ከተፈጸመ ዊዝ ሆልዲንግ ታክስ ሁለት በመቶ ይቀነሳል፡፡
  12. ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 63 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 774 05 76 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  13. የጨረታው አሸናፊ መሆን የሚችለው በተጫረተበት ዘርፍ በጥቅል ዋጋቸው ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውን በመምረጥ ነው፡፡
  14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡ ሆኖም ጨረታዉ በመሰረዙ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ዋጋ ሆስፒታሉ ተጠያቂ አይሆንም፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች የካፌዉን እና የተኝቶ ታካሚዎችን ምግብ ተለይቶ መሙላት አለባቸው፡፡
  2. የካፌዉ ወርሀዊ ኪራይ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ ሆኖ የሚቀርቡ ምግብ እና መጠጦች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መሆን አለበት፡፡
  3. መብራት እና ዉሃ በሆስፒታሉ ካለ የሚቀርብ ሆኖ በሆስፒታሉ በማይኖርበት ጊዜ አሸናፊዉ ገዝቶ የሚጠቀም ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች ለካፍተሪያዉ ከተዘረዘሩት የምግብና የመጠጥ ዓይነቶች በተጨማሪ ከአልኮል ዉጭ በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የቡሬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here