በምሥራቅ ጎጃም ዞን በመርጡለ ማርያም ከተማ አስተዳደር የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ለከፍተኛ የውሃ መስመር ዝርጋታ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸውን ኤች ዲ ፒ እና ዲሲአይ /DCI/ ብረት ቧንቧ በግለፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ወይም ቲን ሰርተፊኬት የሚያቀርብ፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ጥቅል ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ የተረጋገጠ የከፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያውን በጥሬ ገንዘብ ያስያዘ ተጫራች ክፍያውን ለጽ/ቤቱ በማቅረብ በጥሬ ገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ የደረሰኙን ኮፒ ከመጫራቻ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራች የማይመለስ 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 16 ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 4፡00 ድረስ በመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው ከተጫራቾች መመሪያ ጋር የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ በማካተት በእያንዳዱ ገጽ ፊርማና ማህተም በማድረግ ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ በፖስታው ላይ የድርጅቱ ስም፣ አድራሻ ፣ ፊርማ ፣ ማህተም ማድረግና የጨረታ ማስከበሪያ ለብቻ በማሸግና ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ በማሸግና ከላይ የተጠቀሰውን አድራሻ በሙሉ በማጠቃለል ፖስታው ላይ በመጥቀስ በምሥራቅ ጎጀም ዞን በመርጡለ ማርያም ከተማ አስተዳደር የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ16 ቀን እስከ 4፡00 ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም ታሽጎ በ4፡30 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ ያላቸውን አስተያየት የጨረታ ቀኑ ከማለቁ 1 ቀን በፊት ለጽ/ቤቱ አቤቱታ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክር ተጫራች ካለ ከጨረታ ውጭ ሆኖ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ብር ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለተጨማሪ መረጃ ቢፈልጉ በመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 28 59 32 90 /09 12 95 74 39/ በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
የመርጡለ ማርያም ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት