የቢቡኝ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በብ/የሚ/የግ/ግክ ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የአፕል መሰረተ ግንድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉና የብቃት ማረጋገጫ እና የጥራት ስርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- የአፕል መሰረተ ግንድ ማለትም፡- ዝርያ MM 106 ብዛት 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ) ሁኖ የጥራት መስፈርቱ የችግኝ ቁመቱ3 ሜትር እና የተስተካከለ ቀጥ ብሎ የወጣ ችግኙ በሁሉም አቅጣጫ ሥር ያለዉ ከበሽታ እና ተባይ ነፃ የሆነ ከኳራንታይን የጥራት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ እና ዝርያ የሚገልፅ የችግኝ ዉፍረት ከእርሳስ ቅርፅ ያላነሰ እና ያልወፈረ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ የአሰሪው መ/ቤት እና የተጫራቾች ሙሉ ስም አድራሻ ፊርማ ማህተም በማስቀመጥ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት 30 /ሰላሳ ብር/ የማይመለስ በመክፈል ከቢቡኝ ወረዳ ገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ደ/ሃ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 12 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የእቃዉን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቢ/ወ/ግ/ጽ/ቤት/በብ/ሚ/የግ/ማ/ክ ቡድን ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በተከታታይ ከ 27/08/2017 ዓ.ም እስከ 12/09/2017 ዓ.ም 10፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዚሁ ቀን 10፡00 ላይ ይታሸጋል፡፡
- ጨረታዉን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ግብ/ዕ/ቤት/በብ/የሚ/የግ/ግ/ክ ቡድን በቢሮ ቁጥር 06 በ 13/09/2017 ዓ.ም በ3፡00 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መያዝ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን 20 በመቶ የመጨመርም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሚከፍትበት ቀን በዓል እና እሁድ ቅዳሜ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የተጠየቁ ግብዓቶችን በሙሉ ቢቡኝ ወረዳ ፋሲሊደስ ችግኝ ጣቢያ በሙያተኛ ተረጋግጦ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ስለጨረታዉ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 13 79 98 34 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የቢቡኝ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት