ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
64

የጨረታ ቁጥር፡- መ/ግ/ፋ/ግ/ጨ/03/17

በአብክመ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ለቢሮዉ የስራ አገልግሎት የሚውሉ የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን በንግድ ዘርፉ 200,000/ሁለት መቶ ሺህ/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ የጎማ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፣
  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሽህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአብክመ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ቢሮ ቁጥር 37 የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ጨረታው 28/08/2018 ዓ.ም ዓ.ም እስከ 12/09/2017 ዓ.ም የሚቆይ ሲሆን በ 13/09/2017 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጧቱ 4፡00 ይከፈታል ፡፡  ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ  ይከፈታል ፡፡
  9. የጨረታው ግምገማ በሎት/በጥቅል/ እንደሆነ ታሳቢ ይደረግ፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0582200817/0583207434 በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  12. አድራሻ ቀበሌ 8 ባ/ዳር ውኃና ፍሳሽ አገልግሎት ዋና መ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ.37

የአብክመ መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ/ ባህር ዳር

 

 

 

 

 

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here