ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
86

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በድጅታላይዜሽን እና በገቢ ማሰባሰቢያ በጀት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ማለትም 1. Desktop computer  ፣2. Laptop computer ፣3. Mono crom lazer Printer ፣4.Digital Multi function imaging system እና 5.Heavy duty scanner ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ. 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራቾች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በቢሮው ቢሮ ቁጥር 11 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከሚያዚያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክሜንት በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ታሸጐ መቅረብ አለበት፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 08 64 99 67 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here