የአብክመ ሥራ አመራር ኢንስቲትዩት ለ2017 በጀት ዓመት በእቅድ ተይዘው ሳይገዙ የቀሩ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1 የጽዳት እቃዎች ፣ሎት 2 የጽህፈት መሣሪያ ፣ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 4 የመኪና ጐማ በአንድ ጊዜ ውል ተይዞ የሚቀርብ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በኢንስቲትዬቱ ግቢ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን /አገልግሎቶችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ ማስታወቂያ በጋዜጣ /ኦንላይን/ ከወጣበት ቀን ከሚያዚያ 27 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በኢንስቲትዩቱ የግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 19 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ሎት በጨረታ ሰነዱ የሚገለፀውን የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን አንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ በኢንስቲትዬቱ ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ወይም ቢሮ ቁጥር 19 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሚያዚያ 27 ቀን 2017 እስከ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም 4፡00 ታሽጎ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በሥራ አመራር ኢንስቲቲዬት አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የመክፈቻው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን የሚያወዳድረው በድምር ዝቅተኛ ጠቅላላ ዋጋ ነው፡፡
- ኢንስቲትዬቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ ተቀባይነት የለዉም፡፡
- ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 23 60 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሥራ አመራር ኢንስቲትዬት