በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ የምዕ/ጎ/ዞን ጤና መምሪያ ለሰከላ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ለደጋዳሞት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ፣ለቋሪት ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እንዲሁም በ3ቱ ወረዳዎች ውስጥ ለሚገኙ የቀበሌ ጤና ጣቢያዎች አገልግሎት የሚውል ሎት 1 ያገር ውስጥ ፈርኒቸር ፣ሎት 2 ህትመት ፣ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ ፣ሎት 4 የጽዳት እቃ ፣ሎት 5 የቤትና የቢሮ እቃ ፣ሎት 6 መጋረጃና ጠረጴዛ ልብስ ፣ሎት 7 ህንፃ መሳሪያ እና ሎት 8 የኤሌክትሪክ እቃ አቅርቦቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ ጋር በተያያዘው የዋጋ መሙያ መሰረት ዋጋ በመሙላት ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው በቀረበው ዝርዝር መሠረት በእያንዳንዱ ሎት በጥቅል ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ድርጅት ሲሆን በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው ዕቃዎች ለአንድም ዕቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 በመሄድ ለሁሉም ሎቶች የመጫረቻ ሰነድ እያንዳንዳቸውን ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ገዝተው መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ወይም /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ዕቃ ጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና በምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ መምሪያ ስም ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሣቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ክብ ማህተም ፖስታው ላይ በማድረግ ምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በምዕ/ጎጃም ዞን ገ/ኢ/ትብ/መምሪያ በ3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ እለቱ ቅዳሜና እሁድ ወይም ህዝባዊ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ አቅራቢ የውል ማስከበሪያ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ እና እቃዎችን ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/መምሪያ ንብረት ክፍል ድረስ የማጓጓዣ ወጭ ችሎ ማስረከብ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡ የተሻለ አማራጭ ካገኘም ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በማስታወቂያው ላይ ያልተገለፁ ነገሮች ቢኖሩም በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈፃሚ ይሆናሉ፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎችን ናሙና ምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብ/መምሪያ ቢ/ቁ 26 ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ ምዕራብ ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢ/ትብ/መምሪያ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 05 87 75 08 95 በመደወል ማብራሪያ መቀበል ይችላሉ፡፡
የምዕ/ጐጃም ዞን ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብ/ መምሪያ