በእንጅባራ ከተማ የሚገኘው የእዊ ልማት ማህበር ትራንስፈርመር አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማሟላት አለባችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋዮች መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ግዥው ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመግዛት ጠቅላላ ዋጋውን (ታክሱን ጨምሮ) በመመላት በታሸገ ፖስታ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ በመለያየትና በአንድ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ተኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ይከፈታል፡፡
- ጨረታ የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት 10 በመቶ ውል ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለስላቸው አሸናፊው ውል ከያዘ በኋላ ነው፡፡
- ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 227 03 62 /058 227 11 88 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የአዊ ልማት ማህበር