ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
75

የጨረታ ቁጥርአብክመ/ወኩምኤ/ብ/ግ/ጨ/04/08/2017

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት ለአገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም አገልግሎቱ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺ) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር100/መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ምድቦች /ሎቶች/ 1 በመቶ ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም የሚያስይዙት ዋስትና በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎትየተሰጠ ሕጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ከተጠቀሱት ዕቃዎች ተጫራቾችየቴክኒካል እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በተለያዩ ሁለት ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከአንድቴክኒካል እና ከአንድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥና ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ዳይሪክተር ወይም ቢሮ ቁጥር 406 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት በግዥ ንብ/አስ/ዳይሪክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ቁጥር 406 ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጥዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡30 የሚከፈት ሲሆን ቀኑ በዓል ወይም የስራ ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. አገልግሎት መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 406 ድረስ በአካል በመገኘት ወይምበስልክ ቁጥር 058 320 3158 ፋክስ 058 320 1183 ፖ.ሳ.ቁ 965 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አገልግሎት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here