ደብረታቦር ከተማ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2017 የበጀት ዓመት ለማሰራት ካቀዳቸው የመብራት ዝርጋታ የጥገና ስራዎች ውስጥ 1ኛ. ከፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እስከ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ ጽ/ቤት የዋናው መንገድ መብራት ጥገና 2.6 ኪ/ሜትር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የመብራት ዝርጋታ የጥገና ሥራዎች ማስጠገን ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፡-
1. በኤሌክትሮ መካኒካል ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
2. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
3. ያቀረበው ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆንዎን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ከተ.ቁ 1-3 የተዘረዘሩትን መረጃዎች ከዋናው ጋር የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የግንባታ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት የሚቻል ሲሆን የሰነድ መግዣ ዋጋ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይቻላል፡፡
6. ተጫራቾች በአንድ ፖስታ በማሸግ የተጫራቹን ሙሉ አድራሻ ማህተምና የሚወዳደርበትን ፕሮጀክት ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጃ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ሥርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናሉ፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበትን የእቃውን ጠ/ዋጋ ብር 250,000 /ሁለት መቶ አምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም ከስራና ስልጠና መምሪያ ድጋፍ ማስያዝ ይችላሉ፡፡
9. የጨረታ ማከበሪያው ቢያንስ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 /ዘጠና/ ቀን የሚቆይ መሆን አለበት፡፡
10. የጨረታ ሰነድ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ግዥና ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 11/12 ይገኛል፡፡
11. የጨረታ ሳጥኑ መሰረተ ልማት ቢሮ ቁጥር 23 ይገኛል፡፡
12. የግል ኮንትራክተር ያሸነፈበትን ዋጋ ቢያስ 15 በመቶ የመንግስት የልማት ድርጅት ቢያንስ 20 በመቶ ለተደራጁ ኢተርፕራይዞች በሳብ ኮንትራት መስጠት አለበት፡፡
13. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
14. የክልሉን ግዥ መመሪያዎች እስከ ማሻሻያቸው ተግባራዊ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
15. ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ይቆያል፡፡ ውድድሩ በእያንዳንዱ ሎት ድምር መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የእያንዳንዱን ሎት ሁሉንም ዝርዝር ያልሞላ ከውደድሩ ውጭ ይሆናል፡፡
16. ጨረታው በ22ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጐ በ4፡30 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 441 00 91 /00 58 /058 441 02 03 መደወል ይቻላል፡፡
ደብረታቦር ከተማ/አስ/ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ