በምዕራብ ጎጃም ዞን የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውስጥ የሚገኘውን ቁርጥራጭ ብረታብረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም የጨረታውን መስፈርቶች የምታሟሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን / ያላቸው፤ ከ200‚000.00/ሁለት መቶ ሽህ/ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢንድ ቦንድ / ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ግዥውን ግምታዊ ዋጋ መሰረት በማድረግ 20‚000.00 (ሃያ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ /ሲ.ፒ.ኦ / በኮሌጁ ስም ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረታ መቆያ ጊዜ ከ22/11/2016 እስከ 06/12/2016 ዓ.ም ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ይሆናል ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ የጨረታ መወዳደሪያውን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በግዥ ፋ/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 07/12/2016 ዓ.ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበት ቀን የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት በ16ኛው ቀን ማለትም በ07/12/2016 ዓ.ም ሲሆን ከረፋዱ 4፡00 የጨረታ ሳጥን ታሽጎ ተጫራቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በ07/12/2016 ዓ.ም በእለቱ 4፡30 ጨረታው የሚከፈት ሁኖ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058 774 07 71 ደውሎ ወይም በአካል ቀርቦ ማየት ይቻላል፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ውል ከያዘ በኋላ የሚጠበነቅበትን ክፍያ በመክፈል ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት /ግለሰብ/ ማሸነፉ ከተገለፀ ከአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ውል ካልያዘ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይሆናል ፡፡
- ሌሎች በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ነገሮች ካሉ በግዥ መመሪያው መሰረት ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት /ግለሰብ/ የሚዛን እና ሌሎች ወጭዎች በራሱ ሂሳብ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 የማይመለስ 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ