ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
60

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የመስክ ቦርሳ ፣የላፕቶፕ ቦርሳ እና የምኝታ ከረጢት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሟሉ ድርጂቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢነት ሰርቲፊኬት እና የሚገዙ እቃዎች ዋጋ ከ200,000 /ሁለት ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተገለጹትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አብረው ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የመስክ ቦርሳ ፣የላፕቶፕ ቦርሳ እና የምኝታ ከረጢት አይነትና ዝርዝር መግለጫ ጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም ዓይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋውን አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመስሪያ ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን እና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ አማርኛ መሆን አለበት፡፡
  9. በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
  10. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 106/107 በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  11. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ተኛው ተከታታይ ቀን ቆይቶ በ16ተኛው ቀን በ4፡00 ተዘግቶ 4፡30 ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ህዝባዊ በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ሰነዱ በሌሉበት ይከፈታል፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  13. በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡

የገዥ መ/ቤት አድራሻ አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ባህር ዳር ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 058 218 00 14 /058 218 11 03 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

አ.ብ.ክ.መ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here