የወረታ ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽ/ቤት የ2013 እና 2014 የ2 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታው ለመወዳደር ይችላሉ፡፡
- የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ ፤ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር ከፍለው የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሱ፡፡
- ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪዉ አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት ወይም ከኢትዮጵያ ሒሣብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማህበር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ (ተቋሞቹ የሚሰጡ ከሆ)፡፡
- የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በወረታ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ፡፡
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በጽ/ቤታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ከፍለዉ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት “የቴክኒክ ማወዳደሪያ ሰነድ” ፤”የዋጋ ማወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/” ማሲያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያዉ ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያዉ ሰነድ ካለበት ፖስታ ዉስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ዉስጥ ቢሮ ቁጥር 03 ወይም ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸዉ መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከዉድድር ዉጭ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡00 በድርጅቱ ሻይ ክበብ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸዉ ባሉበት ጨረታዉ ይከፈታል ይሁን እንጅ ጨረታው የጨረታ ተወዳዳሪዎች ባይገኙም በተጠቀሰው ሠዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡- ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 የድርጅቱ የስራ ሠዓት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ ከአስፈለገ በስልክ ቁጥር 058 446 05 97 ወይም 09 18 48 46 40 በመጠቀም መጠየቅ ይቻላል፡፡
የወረታ ከተማ ውሀ አገልግሎት ጽ/ቤት