ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
157

ባህር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን በበጀት አመቱ ከሚያሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል 1. የአስፓልት ጥገና ሥራ ከአኮቴት እስከ አዲሱ ሚካኤል አስፓልት ድረስ ያለዉን የአስፓልት ጥገና ሥራ መሳተፍ ለሚልፈጉ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 2 /ሁለት/ እና በላይ የሆኑ፡፡ በጨረታው መጫረት ይችላሉ፡፡

  1. የታደሰ የንግድ የሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ  እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
  2. ከላይ  የተጠቀሰውን  ፕሮጀክት  ለማሰራት  አስፈላጊውን  ሁሉ  የሰው  ሃይል ፣የማቴሪያል እንዲሁም የመሳሪያ አቅርቦቶችን  የሚያሳይ  በስማቸው  የታሸገ  የፋይናንሽያል  እና  የቴክኒካል  የመወዳደሪያ  ሃሳቦችን  ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. የጨረታ  ሰነድ  መግዛት  የሚፈልጉ  ማንኛውም  ህጋዊ  ተጫራች  ባሕር  ዳር  ከተማ  አስተዳደር  መንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 10 ስልክ 058 320 18 78 /058 320 32 46 ፣ አድራሻ ባሕር ዳር መንገዶች ባለስልጣን የማይመለስ  ብር 2,000 /ሁለት ሽህ ብር/ በመክፈል መግዛት ምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች የተጫራቹንና የኘሮጀክቱን ስም በግልጽ ተቀባይነት ባለው የጨረታ ማስከበሪያ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በጨረታ ዝርዝር መረጃ ሰንጠረዥ የተጫራቾች መመሪያ ተ.መ 21.1. ላይ የተጠቀሰውን የገንዘብ መጠን ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች መመሪያ በማንበብ ሙሉ ፈቃደኛ እንዲሆኑ ይመከራሉ፡፡
  1. ኘሮጀክቱ የሚጠናቀቅበት ቀን በክፍል 8 አንቀጽ አ.ዉ.ሁ 72.1 ላይ በተገለጸዉ ቀን መሰረት ይሆናል፡፡
  1. ሁሉም የቅድመ ማጣሪያ /ቴክኒካል/ እና ጨረታ ዋጋ /ፋይናንሻል/ ሰነዶች በተለያዩ ኢንቨሎፓች ማህተም ማድረግ መታሸግ ይኖራባቸዋል፡፡ (አንድ ኦርጅናል አንድ ኮፒ)፡፡
  2. ጨረታው ሁለት የግምገማ ሂደቶች ይኖሩታል፡፡ የመጀመሪያው ሂደት /ደረጃ የቴክኒካል ሰነዶች ግምገማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቴክኒካል ግምገማውን ካለፉት ተጫራቾች ውስጥ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ በቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ኮቢ-01/02 በቀን  15/09/2014 ዓም  በተሻሻለዉ  መመሪያ  መሰረት  የጨረታ  ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች መምረጥ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የተያያዘዉን  መመሪያ በደንብ ያንብቡት፡፡
  3. የታሸጉ የቅድመ ማጣሪያና የጨረታ ዋጋ ሰነዶች የሚያቀርቡት ለመንገዶች ባለስልጣን የግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ሆኖ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ2፡30 ጀምሮ እስከ 16ኛ ቀን ሳጥኑ እስኪታሸግ ድረስ ሲሆን ጨረታው በይፋ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ  ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 3፡00 ታሽጐ 4:00 ላይ በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 13 ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ከሥራ ቀናት ውጭ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
  4. ተጫራቾች ማንኛውንም ተጨማሪ መረጃ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መንገዶች ባለስልጣን ስልክ ቁጥር 058 320 18 78 /058 320 32 46 ደውለው ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. በባሕር ዳር ከተማ በባለፈው አመት ውስጥ ፕሮጀክት ጀምሮ ያቋረጠ ወይም በተሰጠው ውል መሰረት ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች ያሉት ተጫራች በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ አይችልም፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ከሥራ ዝርዝሩ ውስጥ ወይም ከዚህ በላይ የሥራ አይነቶች ላይ የነጠላ ዋጋ ሳይሞላ ቢቀር ያለ ክፍያ ሥራውን እንዲሰራው ይገደዳል፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታውን ከማስገባቱ በፊት የሳይት ጉብኝት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ስለዚህ አሰሪ መስሪያ ቤቱ ከሳይቱ ሁኔታ ጋር የተያያዙ ቅሬታዎችን አይቀበልም፡፡
  8. ማንኛዉም ተጫራች በሚሞላዉ ሰነድ ላይ የሚፈጠር ሥርዝ ድልዝ ከዉድድር ዉጭ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መደበኛ የጨረታ ሰነድ ለግንባታ ሥራዎች ግዥ በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የተዘጋጀ 2011 ዓ.ም መረጃ ከሰነዱ ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ይመልከቱ፡፡
  9. ተጫራቹ ከዚህ በፊት ላከናወናቸው ተመሳሳይ አገልግሎቶች ከአሠሪው አካል የመልካም ሥራ ማረጋገጫ ማስረጃ በቁጥር ቢያንስ (1)አንድ ማቅረብ አለበት፡፡
  10. የባ/ዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር መንገድ ባለስልጣን

ባህር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here