ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
76

በምሥራቅ ጎጃም አስተዳደር ዞን የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የግዥ/ን/አስ/ቡድን ለደ/ኤ/ወ/ጤና ጥበቃ/ጽ/ቤት በአልማ በጀት የማህረሰብ አቀፍ ጤና መድን መዳሀኒት ቤት ለማስገንባት ስለሚፈልጉ ደረጃ GC ወይም BC -7 እና ከዚያ በላይ በሆኑ ተቋራጮች እንዲሁም የደ/ኤ/ወ/ትም/ጽ/ቤት በአልማ በጀት ድጋፍ አማካኝነት ትግል ፍሬ የመ/ጀ/ደረጃ ት/ቤት G+2 የመማሪያ ክፍል ደረጃ GC ወይም BC -6 እና ከዚያ በላይ በሆኑ ተቋራጮች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ተቋራጮች በማወዳደር ግንባታውን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በዘርፉ የተሰማራችሁ ተወዱዳሪዎች፡-

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እንዲሁም ቲን ማያያዝ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው ብር000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሚጫረቱበት ግንባታ በመ/ቤቱ መ/ሂ 1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ በአድራሻ ለደ/ኤ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ብላችሁ የሞሉትን ዋጋ አንድ በመቶ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን በጥሬ ገንዘብ እና በሁኔታ ላይ የተመሰረተ ዋስትና ማስያዝ ከውድድሩ ውጭ ከጨረታ ውጭ ያደርጋል፡፡ በተጨማሪም የሥራና ስልጠና የድጋፍ ደብዳቤ ማስያዝ ከውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
  4. ተጫራቾች በዲዛይኑና በሥራ ዝርዝሩ መሰረት በጥሩ የእጅ ጽሁፍ ሥርዝ ድልዝ ሳይኖረው የምትገነቡበትን ዋጋ በትክክል መሙላት ይጠበቅባችኋል፡፡
  5. ውድድሩ በጥቅል /በሎት መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን /ሰነዱን /በጥንቃቄ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ ዋጋውን በመሙላት በፖስታ አሽጎ ግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ኦርጅናል ኮፒ ለየብቻው በማሸግ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ በአድራሻ ለደ/ኤ/ወ/ገ/ጽ/ቤት በማለት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 31ኛው ቀን 2017 ዓ/ም 4፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 30 ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው በ31 ኛው ቀን 4፡00 ተዘግቶ በእለቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 8 የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 31ኛው ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  11. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከአሰሪው መ/ቤቱ ጋር ውል በመያዝ ወደ ሥራ መግባት ይኖርበታል፡፡ ነገር ግን የዉድድሩ አሸናፊዎች ከመሃንዲስ ግምት 25 በመቶ በላይ የተጋነነ ዝቅተኛ ዋጋ ከሆነ የውል ማስያዣ በመ/ቤቱ መ/ሂ-1 ወይም በባንክ የተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ያሸነፉበትን ዋጋ 25 በመቶ የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  12. ተጫራቾች በስልክ ቁጥር 058 250 04 85 /058 250 00 10 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላሉ፡፡
  13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን 50 /አምሳ ብር/ በመግዛት በሥራ ዝርዝሩ እና ዲዛይኑ መሰረት ዋጋ ሞልተው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  14. የጨረታ ማስከበሪያ አሸናፊ ከተለየ በኋላ ለተጨማሪ 30 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፡፡
  15. ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተካተቱ ነገሮች በክልሉ የግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 እና በመንግስት ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ላይ በተደረገዉ ማሸሻያ መመሪያ ቁጥር አብክመ ገ/ቢ/ከቢ-01/02 በቀን 15/09/2014 ዓም በተፃፈው መመሪያ መሰረት የሚፈጸም ይሆናል፡፡

የደብረ ኤልያስ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here