ለሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት በ2017 በጀት አመት አገልግሎት የሚሰጡ እቃዎች ማለትም ሎት 1 ለተማሪዎች ምግብ የሚሆን ሰርገኛ ጤፍ ፣ሎት 2 የተማሪዎች ምኝታ ፍራሽ እና ሎት 3 የቢሮ እና የተማሪዎች መገልገያ ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር መለያ ቁጥር (ቲን )ያላቸው፡፡
- የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም ያላቸው፡፡
- የጠቅላላ ግዥ መጠን ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ማንኛውም ግዥ ከብር 10000 (አስር ሺህ ብር) በላይ 2 በመቶ ቅድመ ግብር ተቀንሶ የሚቀር ይሆናል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቁ ባንኮች /በሲፒኦ/ አንድ በመቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የጨረታ ውል ማስከበሪያ ማሸነፋቸው በተገለፀ በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከባንኮች የጠቅላላ ግዥ ዋጋ 10 በመቶ /ሲፒኦ/ በማቅረብ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ላይ ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፣የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ቲን ነበር በአንድ በታሸገ ፖስታ አድርገው ት/ቤቱ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 የሥራ ሰዓት ይቆያል፡፡
- ጨረታው በቀን 26/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት በቀን 26/09/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ምርቱን /እቃውን/ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ ት/ቤት ግቢ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
- ት/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ከዚህ በላይ ያልተጠቀሱ የጨረታ መመሪያዎች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፡፡
አድራሻ ፡- ደ/ማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ግቢ ስልክ 09 20 50 43 80 /09 20 50 68 87 /09 37 37 28 10 ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የሐዲስ አለማየሁ ልዩ አዳሪ ት/ቤት