ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
87

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ እቃዎች ፣የኤሌክትሮኒክስ እቃ ፣የፈርኒቸር እቃዎች ፣የጽዳት እቃዎች እና የመኪና እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ መወዳደር ይችላሉ፡፡ ስለዚህ፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የታደሠ የንግድ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤የቫት ተመዝጋቢ የሆነ TIN Numer ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ ሆነው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና ለእቃው ቀጥተኛ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/  በመያዝ ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ ቢሮ ቁጥር 102 ሠነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ በኦርጅናሉ የማወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት አለባቸው፡፡
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን 11/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነድን በመግዛት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በጨረታው ከሚቀርቡ አገልግሎት ከጠቅላላ ዋጋ ላይ ሁለት በመቶ በባንክ በተመሠከረለት ቼክ ወይም /ሲፒኦ/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ማንኛውም ዋጋ የሚሞላውና ክፍያ የሚፈፀመው በኢትዮጵያ ብር ብቻ ነው፡፡
  6. በጨረታው የሚሳተፈው ተወካይ ከሆነ ህጋዊ የሆነ ውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ተጫራቾች በወቅቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
  1. በጨረታዉ አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ተገልጾለት ውል ከወሰደበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ እቃውን ማስረከብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  2. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ቢፈልጉ በስልክ ቁጥር 058 218 14 24 /058 218 06 44 /058 218 00 75 መጠየቅ ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  4. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here