በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ባሕረ መዝገብ እና ልሳነ ፍትህ መጽሔት ህትመት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነዱን ሲሞሉ ሥርዝ ድልዝ የሌለው ሰነድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ህትመት ለማቅረብ የሚሳተፋ አቅራቢዎች የጨረታ ሰነድ ፖስታ ታሽጐ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል አብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ባሕረ መዝገብ ህትመት ብር 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ልሳነ ፍትህ መጽሔት ህትመት ብር 6,000 /ስድስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በአብክመ ፍትህ ቢሮ ከግዥና ፋይ/ንብ/አስተ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማለትም ከ11/9/2017 እስከ 25/09/2017 ዓ/ም ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 04 በ16ኛው ቀን 26/09/2017 ዓ.ም 3፡30 ተዘግቶ በ4፡00 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 226 31 00 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፍትህ ቢሮ