ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
98

በወልድያ ከተማ አስተዳደር የሚገኘው የመንግስት የልማት ድርጅት የሆነው ገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በ2017 በጀት ዓመት ለሚገነባው የፈለገ ህይወት ሪፈራል ሆስፒታል ህንጻ ጥገና ግንባታ ፕሮጀክት OPD FM,SCW BLOCK ጥገና ሥራ ሁሉንም ግብዓቶች በማሟላት መስራት ለሚፈልጉ በዘርፉ የተስማሩ ህጋዊና ብቃት ካላቸው ህንጻ ሥራ ተቋራጭ እና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭ ደረጃ 5 እና በላይ የሆኑ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ከዚህ በታች  የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡-

  1. ተጫራቾች በሥራ ዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ሰርተፊኬት ያላቸውና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ፡፡ ሁሉንም ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ የባንክ ጋራንቲ ኦሪጂናል /ዋና/ ዶክመንት ሰነዶች ጋር አያይዘው አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢሹራንስ ማቅረብ አይቻልም ፡፡
  3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ስነዱን ወልድያ ከተማ ጎማጣ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስ/ር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ላይ ይታሸጋል በሚቀጥለው ቀን ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ በኢንተርፕራይዙ ጽ/ቤት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባይገኙም ጨረታው ከመከፈት አይታገድም፡፡
  4. ተጫራቾች ፋይናንሻል ዋና እና ቅጅ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቶችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች ዋጋ ሲሞላ ቫትንና ሌሎች ታክስ ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት የተከለከለ ነው፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች ቅሬታ ካለው ጨረታው በተከፈተ በ3 ቀናት ውስጥ ማቅረብ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 12 01 40 10 /09 12 91 82 14 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የገነቴ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here