የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለደሴ ወኪል መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ቢያንስ 12 ክፍሎች እና ከዚያ በላይ ያለው ለአንድ ዓመት ክራይ ድርጅቶችን በማወዳደር በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ፣ከመንግስት የሚጠበቅባቸዉን የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸዉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና የግዥዉ መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ለዚህ የተዘጋጀውን ሠነድ በደሴ ወኪል መ/ቤት በአካል በመቅረብ በብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታው ሠነድ ያለምንም ሥርዝ ድልዝ መሞላት ይኖርበታል፡፡
- የተሞላው ዋጋ ቫትን የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ መግለጽ ይኖርበታል፡፡ የተገለፀ ነገር ከሌለው ከቫት ጋር እንደተሞላ ይቆጠራል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዛቸውን የሚገጽ ማስረጃ ከሠነድ ጋር አብሮ አያይዞ መቅረብ አለበት፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይ ሆኖ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 220 89 65 ባሕር ዳር /033 312 00 63 ደሴ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት