የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ ወልድያ ከሃምሌ 1/2017 ዓ.ም እሰከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ሎት 1. ሰርገኛ ጤፍና የተከካ በቆሎ ፣ሎት 2 ፊኖ ነጭ የዳቦ ዱቄት እና ሎት 3. የባልትና ውጤቶች የሚያቀርቡ ነጋዴዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም፡-
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በዚህው የሥራ መስክ ለመስራት የተመዘገቡ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- አሸናፊው አካል በስማቸው የታተመ ደረሰኝ ያላቸው፡፡
- የሚሞላዉ ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ከሆነ ተጫራች /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸዉ፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ የሚቆይበት ጊዜ ከ18/09/17 እስከ 02/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡30 ድረስ ብቻ ነዉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ አንድ በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም /በሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከ18/09/2017 እስከ 02/10/2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከመ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥ የማይመለስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ እስከ 03/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 3፡30 ድረስ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀዉ ሣጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡ ጨረታዉ በዚሁ ቀን 03/10/17 ከረፋዱ 3፡30 ላይ ታሽጎ 4፡00 ላይ እራሣቸዉ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፋበ\ትን እቃዎች በሙሉ በራሳቸዉ ወጭ መ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ሙሉ አድራሻ ማህተም ፊርማና ሌሎችን ማስረጃዎችን አሟልተዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- በጨረታዉ የሚቀርቡ ዕቃዎች በሙሉ ጥራታቸዉን የጠበቁ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የዉል ማስከበሪያ 10 በመቶ በባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- የበለጠ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 331 12 40 በመደወል ወይም በአካል በመቅረብ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የሰ/ወሎ ዞን ማረ/ቤቶች መምሪያ