የነፋስ መውጫ ሆስፒታል የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችል መሆኑን ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ በ2017 ዓ/ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ማስረጃ ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን እና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙትን ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 15ኛው ቀን 11፡00 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ብር የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም ጥሬ ገንዘብ በመሂ/1 በመቁረጥ ማስያዝ ፤ያስያዙበትን መሂ/1 ኮፒ ወይም /ሲፒኦ/ ኦሪጅናሉን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በጥንቃቄ ታሽጎ ፖስታው ላይ ፊርማና ማህተም ተደርጎ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 11፡00 ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ለመክፈት የሚገድብ ነገር አይኖርም፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቆይታ ይኖረዋል፡፡ በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በዚሁ ዕለት 4፡00 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 445 08 87 /09 30 03 34 13 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በጠቅላላ ድምር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን ሲሆን የሁሉም ዕቃዎች ዋጋ መሞላት አለባቸው፡፡
- ሆስፒታሉ ከአሸናፊው ተጫራች ላይ 30 በመቶ የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ዕቃ ከሆስፒታሉ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
የነፋስ መውጫ ሆስፒታል