ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
94

በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 አዲሱ ስታዲየም ፊትለፊት ድጋፌ ህንጻ ጎን የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ 144 መሰረታዊ ማህበራትን የያዘ ህብረት ሥራ ማህበር ሲሆን ማህበሩ እስካሁን ባለዉ የሥራ እንቅስቃሴ በሜካናይዜሽን አገልግሎት በቀን 82 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም ያለዉ የስንዴ ዱቄት ፋብሪካ እና መካከለኛ የመኖ ፋብሪካ አቋቁሞ አባላቱንና የአካባቢዉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል፡፡ አሁን ላይ የሥራ እንቅስቃሴዉን በማስፋት የስንዴ ዱቄት ፋብሪካዉን የዱቄት ምርት በግብዓትነት በመጠቀም መለስተኛ የዳቦ እና ብስኩት ምርት በማምረት አባላቱንና የአካባቢዉን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግ ዕቅድ በመያዝ ወደ ሥራ ገብቷል ዕቅዱን ተፈጻሚ ለማድረግ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ የአዋጭነት ጥናት የህብረት ሥራ ማህበራት ህጎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በማስጠናትና በማስገምገም በአማካሪ ድርጅት ማሰራት ስላስፈለገ አማካሪ ድርጅቶችን ለማወዳደር ይህን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ አዉሏል፡፡ ሎት 1 መለስተኛ የዳቦና ብስኩት ማምረቻ ፋብሪካ አዋጭነት ጥናት ሰነድ ማስጠናትና ማዘጋጀት አገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ሎት 2 ነጭ በቆሎ 20,000 ኩንታል የ2017 ዓ/ም ምርት የሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ሽያጭ ፣ሎት 3 የሮለር ጥርስ ማስወጣት የአገልግሎት ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ ፣ሎት 4 የፋብሪካ ዲናሞ ማስጠቅለል የአገልግሎት ግዥ ለሁለተኛ ጊዜ ፣ሎት 5 የዱቄት ፋብሪካ መለዋወጫ ለ3ኛ ጊዜ ፣ሎት 6 ያገለገለ ዕቃ ባዶ ጆንያ ሽያጭ ለመጀመሪያ ጊዜ ፣ሎት 7 የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ እና ሎት 8 ኤሌክተሮኒክስ ላፕቶፕ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዉል በመያዝ መሸጥ ፣መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅት መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው፡፡
  2. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ /ዋስትና/ ወይም /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅርቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
  3. ግልጽ ጨረታው በብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራች በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና (ሲፒኦ) ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል /ሎት/ የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አለመሆኑ ይታወቅ፡፡
  4. ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  5. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ በማስገባት ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. በጨረታ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት እና ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ጊዜ ለወጣዉ ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 101 ማግኘት ይቻላል፡፡
  7. ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣዉ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ለ2ተኛ እና ለሶስተኛ ጊዜ ለወጣዉ ደግሞ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00  ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ ይከፈታል
  8. ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ተወዳዳሪዎች /ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
  10. የጨረታ አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ አስር በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
  11. አሽናፊ የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን በፍትህ ውል ከተመረመረ (ከተመዘገብ) የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል /ይሸፍናል፡፡
  12. አሸናፊው ዋጋ ሲሞላ የአንድ ኩ/ል በቆሎ ዋጋ ታሳቢ አድርጎ ይሙላ፡፡ አሸናፊዉ ያሸነፈዉን ንብረት ማጓጓዣ ትራንስፖርት እና ጫኝ አዉራጅ ለወዛደር ወጭ አሸናፊው ይሸፍናል፡፡
  1. በአንድ ሎት ዉስጥ ካለዉ ለይቶ መሙላት አይቻልም ሁሉንም አይነት መሙላት ግዴታ ነዉ ማለትም ንግድ ፈቃዱ የማይጋብዝ ካልሆነ በስተቀር፤
  2. የአዋጭነት ጥናት ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በሥራ ሰዓት መርከብ ዩኒየን ዋናዉ ቢሮ ቁጥር 101 በአካል በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ ፡፡
  1. የአዋጭነት ጥናት ማንኛውም ተጫራች የሚያስገባውን ሰነድ የቴክኒካል /Technical/ እና የዋጋ ማቅረቢያ /Financial/ ሰነዶችን በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታ ላይ የተጫራች ስም ፣ፊርማ ፣በትክክል በመፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ሥርዝ ድልዝ ያለው ፣በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ፣የደበዘዘና የማይነበብ ሰነድ ፣የድርጁቱ ማህተም ያልተመታበትና ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር የጨረታ መወዳደሪያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ፣የቴክኒክ መገምገሚያ ነጥቦች ከጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ ይሆናል፡፡ የዳቦ ፋብሪካዉ በሰዓት እስከ 15,000 ዳቦ የማምረት አቅም ያለዉ የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ነዉ፡፡
  2. ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተሰጠውን ዋጋ መለወጥ አይችሉም፡፡ ካሸነፉበት እስከ ሚያስረክቡበት ቀን ድረስ ውሉ የፀና ይሆናል፡፡
  3. በዚህ ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማህበራት የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
  4. ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  5. ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /09 18 08 26 26 መጠየቅ ይቻላል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

  1. ተጫራቾች አማካሪ ተቋማት ይህንን ሰነድ በሚሞሉበት ጊዜ ለእያንዳንዱ ተግባር የሚያስፈልጉ የሰው ሀይል ብዛት ፣ተግባሩን ለማከናወን የሚፈጀው ጊዜ እና ለተግባሩ የተጠየቀው ዋጋ በዝርዝር ማቅረብ አለበት፡፡
  2. እያንዳንዱ በአማካሪ በተቋሙ የሚሰሩ ሥራዎች ዩኒየኑ እንዳስፈላጊነቱ በራሱ ባለሙያዎችም ሆነ በአደራጅ ተቋማት በሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰራውን ሥራ ለማስገምገም በሚፈልግበት ወቅት ሥራዎቹን ማቅረብ እና የሚሰጡ ሙያዊ አስተያየቶችን ተቀብሎ ማስተካከል አለበት፡፡
  3. አማካሪ ተቋሙ እና ዩኒየኑ በጋራ ተስማምታችሁ በሚቀመጠው የጊዜ ፕሮግራም መሰረት የተሰሩ ሥራዎችን ለዩኒየኑ ወይም በዩኒየኑ ሥራውን እንዲገመግምለት ለተወከለው ተቋም ሥራውን አመቺ በሆነ የቴክኖሎጂ አማራጭ ተደራሽ ማድረግ አለበት፡፡
  4. የስራዉ ወሰን፡-
    • ስራዉ መርከብ ሁለ/የገ/ህ/ስራ ማህበራት ዩኒየን ለማቋቋም ላሰበዉ በሰዓት እሰከ 15,000 ዳቦ ማምረት የሚችል የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የአዋጭነት ጥናት ግምገማ ጥናት የሚሰራ አማካሪ ድርጅት መቅጠር ሲሆን ይህም የህብረት ሥራ ማህበራት ህጎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የሚከናወን ይሆናል፡፡
  5. የሚጠበቁ ዉጤቶች፣
    • የአዋጭነት ጥናት ሰነድ፣
  6. የበጀት የጊዜ ሰሌዳና የድርጊት መርሀ ግብር፣
    • የአዋጭነት ጥናት ሰነድ ዝግጅት ተግባራት ለማከናወን የሚያስፈልግ ጊዜና በጀት በእያንዳንዱ ተግባር ተዘርዝሮ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  7. ተጫራች ድርጅት ይህንን ሰነድ በሚሞላበት ጊዜ ለእያንዳንዱ ተግባር የሚስፈልግ የሰዉ ሀይል ብዛት ተግባሩን ለማከናወን የሚፈጀዉ ጊዜ እና ለተግባሩ የተጠየቀዉ ዋጋ በዝርዝር ማቅረብ አለበት፡፡
  8. ሰነዶች በአማካሪ ድርጅቱ በሚሰሩበት ጊዜ የሰነዱን ረቂቆች ዩኒየኑ እንዳስፈላጊነቱ በራሱ ባለሙያዎችም ሆነ በአደራጅ ተቋማት በሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰራዉን ሥራ ለማስገምገም እንዲያስችለዉ ሰነዶቹ የሚገመገሙበትን የጊዜ ሰሌዳ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡
  9. ዩኒየኑ እንደአሰፈላጊነቱ በራሱ ባለሙያዎችም ሆነ በአደራጅ ተቋማት በሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች የተሰራዉን ሥራ ለማስገምገም በሚፈልግበት ወቅት አማካሪ ድርጅቱ በጊዜ ሰሌዳዉ መሰረት ሥራዎቹን ማቅረብ እና የሚሰጡ ሙያዊ አስተያየቶችን ተቀብሎ ማስተካከል አለበት፡፡
  10. የአዋጭነት ጥናት ሰነዶች የሚዘጋጁት በእንግሊዘኛ ቋንቋ መሆን ይኖርበታል፡፡

መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ዩኒየን ኃ.የተ

 

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here