ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
109

ቁጥር ግጨ 01/2017

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ለአዲ-አርቃይ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለውሃ ፓምፕ አገልግሎት የሚውሉ ሶላር ፓኔል እና አክሰሰሪ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤ የእቃው ግዥ መጠን ከ200,000.00 (ከሁለት መቶ ሽህ ብር)  በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ15 ቀናት ገንዘብ ቢሮ ከሚገኝበት ባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 03 ከዲፓ መስመር ዝቅ ብሎ ቢሮ ቁጥር 101 ወይም 102 በአካል በመቅረብ የማይመለስ 250.00 (ሁለት መቶ አምሳ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይቻላል፤ ሰነዱን ከገዙ በኋላ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም ፊርማና አድራሻ በትክክል በመሙላት በመሥሪያ ቤቱ  ለዚህ ጉዳይ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የገዙትን የጨረታ ሰነድና አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ አየር ላይ ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00  የጨረታ ሳጥኑ ይዘጋና በዚሁ ዕለት 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባሕር ዳር ከተማ በሚገኝው የአብክመ ገንዘብ ቢሮ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 ላይ ይከፈታል፡፡
  4. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም በቢሮው የጨረታ ገምጋሚ ኮሚቴዎች የጨረታ ሳጥኑ የሚከፈት መሆኑን እንገልጻለን፡፡ 16ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እና እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይዘጋና ይከፈታል፡፡
  5. ተጫራቾች የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮው ገንዘብ ያዥ በኩል ደረሰኝ በማስቆረጥ የደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በጨረታው ፓስታ ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋጅበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን አለበት፡፡
  7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. የሚገዙ እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን)፤ መመሪያዎችና የውል ቃሎችን እንዲሁም የዋጋ መሙያ ቅጾችን ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተዘጋጅተው የቀረቡ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
  9. ለበለጠ መረጃ በአብክመ ገንዘብ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 108 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 13 56/058 220 08 39 በመደወል ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here