ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
76

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በዩኤንዲፒ ድጋፍ በጀት Desktop computer ግዥ ለመፈፀም በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ውል በመያዝ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ፡-

  1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  3. የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ በመሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ በተ.ቁ.1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው በታሸገ በፖስታ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ነገር ግን ከላይ ከ1-3 የተጠቀሱትን ያላቀረቡ ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተ/ዳይሬክቶሬት በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 01 ማግኘት ይቻላል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመሙላት በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ቢሮ ቁጥር 11 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ከመክፈቻ ቀንና ሰዓት በፊት ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በመ/ቤቱ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  8. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከግንቦት 18 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ሰኔ 02 ቀን 2017 ዓ/ም ድረስ ለተከታታይ 15 ቀን በጋዜጣ ወጥቶ የሚውል ሲሆን በ16ኛው ቀን ሰኔ 03 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  9. ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክሜንት በተለያየ ፖስታ ለየብቻ ታሸጐ መቅረብ አለበት፡፡
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በባሕር ዳር ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09 08 64 99 67 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላል፡፡

የአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት

ባሕር ዳር

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here