ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

0
78

ለወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውሉ የተበላሹ ልዩ ልዩ የX-ray ማሽኖች፣ የተለያዩ የላብላቶሪ ማሽኖች፣ የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎች ብልሽት ለማስጠገንና የጀኔሬተር አውቶማቲክ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ወይም ማስጠገን እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ፡-

ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላችሁ እና የዘመኑን ግብር የከፈላችሁ፡፡

ንግድ ፈቃድና ሌሎች አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ብር ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ከጨረታ ሰነዱና ከታሸገው ፖስታ ላይ የድርጅት የማተም ተነባቢ በሆነ መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡

ተጫራቾች ያሸነፉበት የሥራ (የእቃ) ዋጋ ድምር ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ 2 በመቶ ተቀንሶ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡ መ/ቤቱ ቫት ይሰበስባል፡፡

ተጫራቾች የሞሉትን የዋጋ አንድ መቶ በጨረታ ማስከበሪያ /ቢድ ቦንድ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወይም ከተፈቀደላቸው ባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ በማሲያዝ ከፖስታው ውስጥ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነዱን በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡

የጨረታው አሸናፊ  ማሸነፉ ከተረጋገጠ  በኋላ ማሻሻያ ማድረግ እና ከጨረታ እራሱን ማግለል አይቻልም፡፡

የጨረታ ሰነድን ዝርዝር ማብራሪያ ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል፡፡

ተጫራቾች የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ያወጣውን ግዥ አፈጻጸም መመሪያ አዋጅ ቁጥር 1/2003 እና ተሻሽለው ለወጡ መመሪያዎችና አዋጆች ተገዥ መሆን ይገባቸዋል፡፡

የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ከ18/9/2017 ዓ.ም እስከ 2/10/2017 ዓ.ም ድረስ ባሉት ተከታታይ ለ15 ቀናት በወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግዥ ኦፊሰር ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን እስከ 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በ02/10/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ የጨረታ ሳጥኑ በዚህ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመመሪያው መሰረት የሚከፈት ይሆናል፡፡

ተጫራቾች ጨረታ በሚከፈትበት ወቅት ባይገኙም በመመሪያው መሰረት ይከፈታል፡፡

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል  የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስራ ሂደቱ ስልክ 033 331 01 72 እና 033 331 02 52 ደወሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

የጨረታ መክፍቻ ቀን በዓል ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል፡፡

አሸናፊው ማሸነፉ ተነግሮት ውል ከወሰደ በኋላ ሆስፒታሉ በሚያዘው መሰረት መስራት ወይም መጠገን አለበት፡፡

አሸናፊው ድርጅት ውለታ ከወስደበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ቀናት ወስጥ መጠገን ወይም መስራት አለበት፡፡

የተጠቀስውን ማሽን ጥገና ስራ ግብዓት ቢያስፈልግ በጨረታ አሽናፊው የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ወድድሩ በሎት ድምር ነው፡፡

የወልዲያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here