የፍኖተ ሰላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚዉል የተለያዩ ዕቃዎችን ማለትም ሎት 1. ቧንቧና መገጣጠሚያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል:: ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ ቲን/ ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን ከብር 200‚000 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ በላይ ለሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ::
- የተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በዉሃ አገልግሎቱ ደረሰኝ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች ከ 1-5 የተዘረዘሩትን ማረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ::
- የጨረታ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ይዉላል፡፡ በ15ኛዉ ቀን 11፡30 ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡ በ16ኛዉ ቀን ከጧቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ቢገኙም ባይገኙም ጨረታዉ በግልጽ ይከፈታል፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች ሀሳቡን በአንድ ወጥ በሆነ ፖስታ በጥንቃቄ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰአት ማስገባት ይችላሉ፡፡
- በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማስገባት አይቻልም::
- የጨረታ መክፈቻዉ ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራቾች ከአሸናፊዉ ጋር ዉል እንደተያዘ የጨረታ ማስከበሪያዉ ይመለሳል፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር ለእያንዳንዳቸው ብር 200/ ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 2 ዘወትር በስራ ሰዓት መዉሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ያሸነፈበትን የሎት ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ የዉል ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /በጥሬ ገንዘብ/ ለፍኖተ ሰላም ከተማ ዉሃና ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት አስይዘዉ ዉል በመፈጸም ያሸነፉትን ዕቃ ፍ/ሠ/ከ/ዉ/ፍ/ አገ/ጽ/ ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸዉ፡፡
- ተመሳሳይ የሆኑ እቃዎች በአንድ ምድብ /ሎት/ በማድረግ ዉድድሩ የሚገለጸዉ በጠቅላላ የድምር ዉጤት ነዉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
- በጨረታዉ መሰረዝ ምክንያት ተጫራቾች ላወጡት ወጪ መ/ቤቱ ኃላፊነትን አይወስድም፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ 0587751387/0075 /0923426123 ደዉለዉ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የፍኖተ ሠላም ከተማ ዉኃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት